Pr,tex,bu,vic

Pr,tex,bu,vic


የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2012
በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ገቢዎች የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2012 በጀት ዓመት የተለያዩ

የጽህፈት መሣሪያዎች፤
የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣
የደንብ ልብስ፣
የተለያዩ የቢሮ ቋሚ እቃዎች፣
የህንፃ ቁሳቁስ መገጣጠሚያዎች፤
የተለያዩ ህትመቶች፣
የጥበቃ ቤት ማማ ከላይና ከታች ያለው እና የመኪና እቃዎች፤ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፣

የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ በአቅራቢዎች ዝርዝር ወስጥ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሠርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 / ሃምሣ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ጨምሮ ከጦር ኃይሎች ወደ ቶታል በሚወስደው መንገድ በቀለ እሸቴ ሕንፃ ውስጥ በሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ገቢዎች ባለሥልጣን የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 406 በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሠነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በመ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ ብር 5,000.00 / አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO./ ወይም የባንክ ዋስትና በጽ/ቤታችን ማለትም በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ገቢዎች ባለሥልጣን ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት (ADDIS ABABA CITY GOVERNMENT REVENUES AUTHORITY KOLFE KERANIO SUB-CITY SMALL TAXPAYERS BRANCH OFFICE) ስም በማስያዝ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከ15/07/2012 እስከ 26/07/2012 ዓ. ም 6 ፡30 ሠዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
የጨረታ ሣጥኑ በ7/9/2012 ዓ. ም በ7 ፡00 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤታችን የግዢና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ክፍል ውስጥ ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በሙሉ ወይም በከፊል በመጫረት ይችላሉ፡፡
አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት መስፈርቶች ውጭ በሰነዱ ላይ ባለው መመሪያ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-369-08-56 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ገቢዎች

ባለሥልጣን የኮ/ ቀራንዮ ክ/ ከተማ

አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ / ቤት

_______________________________
Category : Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Construction and Construction Machinery, Construction Raw Materials, Office Supplies and Stationery, Office Items and Equipment, Stationery Supplies, Printing and Publishing., Printing and Publishing Service, Purchase., Textile and Leather Products, Textiles/ Fabrics and Wearing, Vehicle and Spare Parts, Spare Parts Sale and Supply

Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 15፥ 2012
Deadline :2020-04-26

Report Page