Print janitor cheffe2

Print janitor cheffe2


Eid Mubarak!

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨፌ ኦሮሚያ ጽ/ቤት የ2013 ዓ.ም አጀንዳ ህትመት እና የጽ/ቤቱን ሕንፃ እና ቅጥር ግቢውን የጽዳት አገልግሎት በሚሰጡ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ፡-

ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንደዚሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የማ ይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ ብር) በመክፈ ል ከጽ/ቤታችን አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 18 ለዚህ የተዘጋጀውን ዶክመንት መግዛት ይችላሉ፣
የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋበመሙላት በሰምበታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እስ ከ 16 ኛው ቀን ከጠዋቱ አራት ሰዓት 4 ፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ግዢ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
የመወዳደሪያ ዋጋው ከቫት ጋር ወይም ያለ ቫት መሆኑ መገለጽ አለበት፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16 ኛው ቀን በ4 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ4:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል:: 16 ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ፣ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል::
ተጫራቾች ለመወዳደር ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ዶክመንት ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
የአጀንዳ ህትመት ተጫራቾች የራሳቸውን ናሙና ማህተም መለያ/ አድርገውበት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የጽዳት አገልግሎት የሚሰጡ ተወዳዳሪዎች በዚህ ሥራ በቂ ልምድ ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ከዚህ በፊት ጽ/ቤቱ ያወጣቸውን ጨረታዎች አሸንፈው ዕቃውን በወቅቱ ገቢ ማድረግ ወይም ተወዳድረው ያሸነፉበትን አገልግሎት ማቅረብ ያልቻሉና ከተራ ቁ. ከ1-7 የተገለጹትን ያላሟሉትን ጽ/ቤቱ ከጅምሩ ከጨረታው ውጪ ማድረግ ይችላል፡፡
ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ በተገለጸላቸው በ5 ቀናት ውስጥ በጽ/ቤቱ ተገኝተው ውል መዋዋል አለባቸው፡፡
ጽ/ቤቱ ሌላ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ:- ሳር ቤት አካባቢ ከኦሮሚያ ቢሮዎች ፊት ለፊት ነው:: ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0113 71 66

11 መጠየቅ ይቻላል፡፡

የጨፌ ኦሮሚያ ጽ/ ቤት



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 14 ቀን 2012

Deadline: June 6, 2020


© walia tender

Report Page