Print birana 2

Print birana 2


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 08/2012

ብራና ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ ለህትመት አገልግሎት የሚውሉ ጥሬ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የሀገር ውስጥ ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል።

ማንኛውምተጫራች በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊየንግድፈቃድ፣ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይ መለስ ብር 200.00 ( ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ 700 ሜትር አካባቢ በሚገኘው ዋና መ/ቤት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት እንዲሁምቅዳሜን 6ሰዓትጨምሮ ቢሮቁጥር 32 መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በድርጅቱ ስም በባንክ በተረ ጋገጠ ቼክ (CPO) ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ኛው የሥራ ቀን 9 ፡00 ሰዓት ድረስ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 24 በመቅረብ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የዋጋ ማቅረቢያቸውን ማስገባት ይችላሉ።
ማንኛውም ተጫራች የዕቃውን የማስረከቢያ ጊዜ መጠቀስ አለበት።
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበ ት በ11 ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት በዋናው መ/ ቤት በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከድርጅቱ መጋዘን ድረስ ለማቅረብ ያካተተ መሆን አለበት።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ 700 ሜርት ላይ

ስልክ ቁጥር: 011-4426480

ፖ. ሣ. ቁ.22457

አዲስ አበባ

ብራና ማተሚያ ድርጅት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 13 ቀን 2012

Deadline: June 3, 2020


© walia tender

Report Page