Print addis reve3

Print addis reve3


Only 3 Days left,save 25% subscribe now ! enjoy our discount access unlimted tenders all the time! contact walia tender team +251919415260 / +251942125616

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር፡ 003/2012

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሚከተለውን የህትመት አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት አንድ- ህትመት / የመጽሔት ህትመት/
በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የቴክኒክ ፕሮፖዛል “አንድ ኦርጅናል ኮፒ እና የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር “አንድ ኦርጅናል ኮፒ የድርጅቱ ስም፣ አድራሻ እና ማህተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት ሎት በመፃፍ እና በየሎቱ በመለየት በታሸገ በኤንቨሎፕ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ኛው ቀን ድረስ ከቀኑ 11 ፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ እለት ከቀኑ 11 ፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11 ኛው ቀን ( በሚቀጥለው የስራ ቀን) ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት በግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 2012 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ጠቅላላ ከሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ ለሎት አንድ /በሚወዳደሩበት ሎት/ 2% በባንክ በ ተመሰከረለት ቼክ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያያዘው ማቅረብ አለባቸው። CPO መስራት ያለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በሚል አድራሻ መሆን አለበት፡፡
ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመ ለስ ብር 100.00/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊትለፊት አማጋ ህንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አስተዳደር ቡድን በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተ.እ.ታ/ቫት/ ጨምሮ ወይም ተፈታ/ቫት/ በፊት መሆኑን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል። ያልተገለፁ ከሆነ ተ.እ.ታ/ቫት ጨምሮ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀባቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በጨረታው ሰነዱ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውለታ ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም እቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት ናሙናዎችን ለግዥ አስተዳደር ቡድን ማስገባት አለባቸው፡፡
አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፋባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ለጨረታ ከቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% /ሃያ ፐርሰንት ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡በስልክ ቁጥር፡ - 0115 57 57 42 / 0115 57 57 19 በመደወል ወይንም ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት አማጋ ህንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አስተዳደር ቡድን በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ገቢዎች ቢሮ የሪከርድ

ስራ አመራር



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 13 ቀን 2012

Deadline: June 3, 2020


© walia tender

Report Page