Print Gondar Univ3

Print Gondar Univ3

Walia Tender

ባነር እና ማህተም ህትመት አገልግሎት ግዥ

ድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2013 በጀት ዓመት ለዩኒቨርሲቲው አገልግሎት የሚውል ባነር፣ የስም ቲተር እና ክብ ማህተም ህትመት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ አውጥተው ከተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች፤

በዘርፉ የወጣና ለዘመኑ የታደሠ የንግድ ሥራ ፈቃድ ኮፒ ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ኮፒ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርፊተኬት ኮፒ፣ በአቅራቢነት በኤጀንሲው ድረ-ገጽ የተመዘገቡ፤ በማንኛውም የመንግስት ግዥ ጨረታ እንዲሳተፉ በሃገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤ ኮፒ፣ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የገቡበት ቅጽ ሞልተው ፤ ፈርመው እና በድርጅታቸው ማህተም አረጋግጠውና ዋናውን ማቅረብ አለባቸው።
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ብር 25,000.00 / ሃያ አምስት ሺ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ ሲፒኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስም አሰርተው ማቅረብ አለባቸው። በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ከ88 ቀን በታች መሆን የለበትም::
ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ እንዲሁም የዋጋ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናሻል ኦርጅናልና እና ፋይናሻል ኮፒ በማለት ተለይቶ በተለያየ ፖስታ በማሸግና በማያሻማ ሁኔታ በጀርባው ላይ ፋይናሻል ኦርጅናል እና ፋይናሻል ኮፒ በሚል ቃል በጽሁፍ በማመላከትና በድርጅታቸው ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ሁሉም ሶስቱም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ ተጠቃለው ታሽገውና በድርጅቱ ማህተም ተረጋግጠው መግባት አለባቸው።
ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፋይናንስና በጀት ዳይሬክቶሬት ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 07 ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::
ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነዳቸውን ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ይህ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ:: ጨረታውም ታዛቢዎችና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት 4 ፡01 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4 ፡10 ሰዓት ጀምሮ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ህንፃ ላይ በሚገኘው የስልጠና (ኤች.ዲፒ) አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም 16 ኛ ቀን የህዝብ ወይም የሃይማኖት በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት እና ቦታ ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ 60 ቀን ድረስ ጸንቶ መቆየት አለበት፡፡
አሸናፊው ተጫራቶች /አቅራቢው ውሉን ከወሰደ ጊዜ ጀምሮ ከዩኒቨርሲቲው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ብቻ በሚሰጥ ትዕዛዝ ማቅረብ አለባቸው።
ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋ ጨምሮ መሆን አለበት። የታክስ ሁኔታ ያልተገለጸ ከሆነ የተሞላው ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ታክስና ወጭን አካትቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያያዘው ስፔስፍኬሽን በተጨማሪ ቴክኒካል ሰነድ እና ካታሎግ ማቅረብ አለባቸው::

ተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 058-211-80-84 ወይም 058-211-60-92 በስራ ሰዓት በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

***ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡


ጎንደር ዩኒቨርሲቲ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 30 ቀን 2012

Deadline: June 22, 2020


© walia tender

Report Page