Print ACSI1

Print ACSI1

ADMIN3 SELAMAWIT

የጨረታ ማስታወቂያ

አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም የተለያዩ ህትመቶች በጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበወን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ነጋዴ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የጨረታው መመሪያ

በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቶች የ2012 የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር መክፈያ ሰርቲፊኬት
ተጫራቾች ለሚሳተፉባቸው እቃ ኣይነት ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በዋጋ መሙያ መሙላት ይገባቸዋል፡፡ በነጠላ ዋጋና በድምሩ ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋው የሚያዝ ይሆናል፡፡ ዋጋ ሲሞላ ስርዝ ካለ ፊርማ ሊኖረው ይገባል፡፡ ሆኖም ግን ስርዝ ድልዝ ከበዛበትና ግልፀኝነት ከጐደለው ተወዳዳሪው ከጨረታው ይሠረዛል፡፡
ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የኣጠቃላይ ዋጋውን 2% ሲፒኦ / CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የ80 ቀን በኣማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ትከከለኛ ስም በማሰራት ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
ጨረታው ወቅቱ ተጠናቆ ያላቀረበ ማንኛውም ማስረጃ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ስዓት ከሰኞ እስከ አርብ 2:30-11:30 እና ቅዳሜ እስከ 6፡30 የማይመለስ ብር 100.00/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከተቋሙ ሂሳብ ከፍል ቢሮ ቁጥር 403 ወይም አዲስ አበባ ፒያሳ ቀይ ባህር ኮንደሚኒየም በሚገኘው ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡

የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ኛው ቀን ባህርዳር በሚገኘው በአብቁተ ዋና መ/ ቤት ቢሮ ቁጥር 205 ከቀኑ 4 ፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ተግባር ከተዘጋጀው ሳጥን በኢንቨሎፕ በማሸግ የተወዳደሩበትን የጨረታ አይነት የድርጅቱን ስም እና አድራሻ በመፃፍ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ጨረታው በዚህ እለት ከጠዋቱ 4 ፡30 ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልፅ ይከፈታል፡፡

ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ:- ባህርዳር ቀበሌ 10 05822660o8
አዲስ አበባ 0111576740

የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 27ቀን 2012

Deadline: June 18, 2020


© walia tender

Report Page