Print 2 abay insurance12..

Print 2 abay insurance12..

Walia Tender

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ዓባይ ኢንሹራንስ አ..ማ ለ2013 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ አጀንዳዎች እና የጠረጴዛ ካላንደሮች አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ስራውን ለመስራት ፍላጎቱና ብቃቱ ያላችሁ ድርጅቶች የሚከተሉትን የጨረታ መመሪያዎችን በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. ኩባንያው በጨረታ የሚገዛቸው የህትመት ዓይነት የሚከተሉት ናቸው::

1.1 አጀንዳ ……………………..ብዛት…………………3,000

1.2 የጠረጴዛ ካላንደር …….…..ብዛት ……………..2,500


2. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፤የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው:: እነዚህ ሰነዶች በቴክኒካል ኘሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ከነመመሪያው የማይመለስ ብር 100 ( መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኩባንያው ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ ከሚገኘው ሃብት አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ይሆን ዘንድ የጨረታው ን 2 በመቶ (2%) በባንክ ክፍያ ማዘዣ( ሲ. ፒ .ኦ) ወይም የባንክ ዋስትና ማረጋገጫ ደብዳቤ ይዘው መቅረብ ይገባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው በቴኒካል ኘሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳባቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በማለት በግልፅ ከፋፍለው በተለያየ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የቴክኒካል መወዳደርያ መስፈርቶች በጨረታ ሰነዱ ላይ ይገለፃሉ።

6. ጨረታው ከግንቦት 10 ቀን 2012 ዓ. ም እስከ ግንቦት 25 ቀን 2012 ጧት 3 ፡00 ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በእለቱ ግንቦት 25 ቀን 2012 ጧት ጧት 3 ፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡

7. አሸናፊው ተጫራች ከኩባንያው ጋር የአፈፃፀም ውል ይዋዋላል፡፡

8. ኩባንያው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

9. ለተጨማሪ ማብራርያ በስልክ ቁጥር 251-11-553 58 08 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡ አትላስ አካባቢ የሚገኘው የዓባይ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ. ማ ዋና መ/ ቤት

የሃብት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ቁ. 404

በስልክ ቁጥር 011672 50 09 / 251-11-553 58 08 ?

ዓባይ ኢንሹራንስ አ. ማ.




Posted:ሪፖርተር  ግንቦት 09 ቀን 2012

Deadline: May 26, 2020


© walia tender

Report Page