Pr tex sale vic addis5

Pr tex sale vic addis5


ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አ / አ / ከ / አ / ሰ / ፀ / አስ / ቢሮ
እቃ /02/2012 ዓ / ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ለ2012 በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 የደንብ ልብስ ጫማና ልዩ ልዩ እቃዎች፣
ሎት 2 ልዩ ልዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣
ሎት 3 የፅዳት እቃዎች፣
ሎት 4 ህትመት፣
ሎት 5 ልዩ ልዩ የመኪና እቃዎች፣
ሎት 6 ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
ስለሆነም ጨረታውን መካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የንግድ ምዝገባ ወረቀት ያላቸው የዕቃ አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ቲን እና /VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ የማይመለስ ብር 100,00/ አንድ መቶ/ በመከፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ደንበል ሲቲ በሚገኘው በሊፍት 6/ 10ኛ ፎቅ ከመ/ቤቱ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ::
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሚወዳደሩበት ሎት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና /unconditional/ በመ/ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የኢንሹራንስ ዋስትና አንቀበልም፡፡
ሎት 1. የደንብ ልብስ ጫማና ልዩልዩ አልባሳት--ብር 10,000.00 ( አስር ሺ)
ሎት 2 ልዩ ልዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች ብር 3,000.00(ሶስት ሺ)
ሎት 3 የፅዳት እቃዎች ብር 2,000.00(ሁለት ሺ)
ሎት 4 ህትመት -ብር 1,000.00 (አንድ ሺ )
ሎት 5 ልዩ ልዩ የመኪና እቃዎች-- ብር 5,000.00 (አምስት ሺ)
ሎት 6 ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችብር 3,000.00 (ሶስት ሺ )
4 ተጫራቶች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው በመፈረም እና ህጋዊ ማህተም በማድረግ ኦርጅናል እና ኮፒ በየሎቱ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተራ ቁጥር 3 በተጠቀሰው አድራሻ የመ/ቤቱ ግዥ ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 4 ሰአት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በመ/ቤቱ ዋጋመሙያ ያልተሞላ ዋጋፊርማና ማህተም የሌለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

5. ጨረታው በ10 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ላይ ታሽጎ በ10 ኛው ቀን 4 ፡30 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡ ናሙና ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች በሚጫረቱበት እያንዳንዱ እቃ ጥራት በቴክኒክ ብቃታቸው የተመረጡ በዋጋ የሚወዳደሩ ይሆናል :: አማራጭ ጨረታ አይፈቀድም ::

7. አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት ጠቅላላ እቃዎች ዋጋ 10 በመቶ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ አሸናፊነቱ ከታወቀበት ከ7ኛ ቀን ጀምሮ በ 7 ቀናት ውስጥ ውል መፈረም አለበት ::

8. በተራቁጥር 7 መሰረት ውል የማይፈጽሙ አሸናፊዎች ለጨረታ ማስከበሪ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ስማድረግ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ መጠቀም ይችላል፡፡

9. አሸናፊ የሆነ ድርጅት አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት 5ኛ ፎቅ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ለመ/ቤቱ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 0115-62-15-24 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 13 ቀን 2012

Deadline: May 30, 2020


© walia tender

Report Page