Pr p1

የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር AAPPKA 002/12
በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የፖሊስ አካዳሚ ዳይሬክቶሬት ለ2012 በጀት ዓመት በማሰልጠኛ ማዕከሉ ስሩ ለሚገኙት የስራ ክፍሎች ባለው በጀት
ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች
ሎት 2 የፅዳት እቃዎች
ሎት 3 የኤሌክትሪክ እና የግንባታ እቃዎች
ሎት 4 የህትመት ውጤቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
በመሆኑም በዚህ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
ጨረታው የሚከናወነው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግዥ አዋጅ በተገለፀው ግልፅ ጨረታ ስነ-ስርዓት መሰረት ይፈጸማል፡፡ የፅህፈት መሳሪያዎች ፤ የፅዳት እቃዎች ፤ የኤሌክትሪክ እና የግንባታ እቃዎች እንዲሁም የህትመት ውጤቶች ጨረታው የሚያከናውነው ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች እና ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ በ2012 ዓ/ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልፅ ወቅታዊ ደብዳቤ Tax clearance ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር እንዲሁም እታ | VAT | ሰርተፍኬት እና ቲን | TIN / ሰርተፍኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችል ይሆናል ።
ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የኢትዮጵያ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር | ከፍለው የጨረታውን ሰነድ ቢሮ ቁጥር 16 እና 18 መውሰድ ይችላሉ ። በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሰረት የተቋቋሙ ተቋማት ለጨረታው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት የተቋቋሙበት የህጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለ ክፍያ በነፃ ይሰጣቸዋል ::
ተጫራቾች በሎት 1 ብር 2,000.00 / ሁለት ሺህ ብር / ፣ በሎት 2. ብር 3,000.00/ ሶስት ሺህ ብር / በሎት 3 ብር 1,500.00 ( አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ) እና በሎት 4 ብር 500.00 | አምስት መቶ ብር | የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠለት ሲፒኦ በፖሊስ አካዳሚ ዳይሬክቶሬት ስም አዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል ::
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፖሊስ አካዳሚ ፋይናንስና ግዥ ዲቪዚዮን በመቅረብ ለዚህ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው:: ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም ፤
የጨረታው ሳጥን በ11 ኛው ቀን በ 4 ፡ 00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፖሊስ አካዳሚው አዳራሽ ከጠዋቱ 4 ፡30 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል የመዝጊያውና የመክፈቻው ቀን የመንግስት ስራ ቀን ሳይሆን ቀርቶ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ስራ ቀን ይሆናል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡ - 0112 739486 0112739158 0112739548 ወይም _0118-33-38-89 እና 0118-33-3845 መደወል ይችላሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የፖሊስ አካዳሚ ዳይሬክቶሬት
_______________________________
Category : Building Materials, Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Construction and Construction Machinery, Construction Raw Materials, Electrical and Electronics, Electronics Equipment, Office Supplies and Stationery, Office Items and Equipment, Stationery Supplies, Printing and Publishing., Printing and Publishing Service, Purchase.
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 20 ፥ 2012
Deadline :2020-04-08