Pr fu jan st vi
ብሄራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር
EFMHACA/FSD/NCB/ ANNUAL PROCUREMENT/008/2012
የኢትዮጵያ የምግብ የመድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ ጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ በዘርፉ ፈቃድ እና ብቃት ያላቸው ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ህጋዊ ሰነዶች እና በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ ::
ተጫራቾች የ2012 የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ እና Anti bribery pledge form ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤ ቢያንስ እስከ ጨረታው መከፈቻ ዕለት ድረስ የሚያገለግል መሆን የሚኖርበት ሲሆን የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበትን የድጋፍ ደብዳቤ የሚያቀርብ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 150 አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከባለስልጣን መ/ቤቱ አዲሱ ቢሮ 1ኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው ከግዥና አቅርቦት ኬዝ ቲም ቢሮቁጥር 202 መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በግዥና አቅርቦት ኬዝ ቲም በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከዚህ በታች ለእያንዳንዱ ጥቅል (ሎት) የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ቼክ፣ጥሬ ገንዘብ፣ባንክ ዋስትና፣ ወይም CPO በFood, Medicine andHealthcare Administration and Control Authority of Ethiopia ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው። ኢንሹራንስ ቦንድ ተቀባይነት የለውም፡፡ በትክክለኛው የመ/ቤታችን የእንግሊዝኛ ሙሉ ስም ያልቀረበ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
5.1 ሎት 1 አላቂ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ብር 5,000.00 ፣ ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች ብር 5,000.00 ፣ ሎት 3 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ተዛማጅ እቃዎች ብር 10,000.00 ሎት 4 የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮች ብር 10,000.00 ፡ ሎት 5 የጥገና መሳሪያዎች ብር 3,000.00 ፣ ሎት 6 የተሽከርካሪ እቃዎች ብር 7,000.00 ሎት7 የህትመት ስራዎች ብር 10,000.00
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
በመንግስት የተደራጁ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የመንግስት ግዥ መመሪያ በሚፈቅድላቸው መሰረት ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ ከአደራጃቸው ተቋም በመ/ቤታችን ስም የተጻፈ ህጋዊ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በጨረታ ማስከበሪያ ምትክ በመ/ቤታችን ስም የተጻፈ ዋናውን ህጋዊ ደብዳቤ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ ማንበብ አለባቸው፡፡
ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16 ኛው ቀን ከቀኑ 8 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8 ፡30 ሰዓት በጨረታ መከፈቻ ስነሥርዓት ላይ ለመገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባለስልጣን መ/ቤቱ አዲስ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል ፡፡
የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበአል ቀን ከሆነ የመከፈቻው ቀን በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን ይሆናል፡፡
መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር፡ 011 86974 99 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ : አፍሪካ ጎዳና፣ ቦሌ መንገድ ወሎ ሰፈር አካባቢ
የኢትዮጵያ የምግብ የመድኃኒትና
ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባስልጣን
_______________________________
Category : Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Furnitures, Office Furniture, Installation and Maintenance, Printing and Publishing., Printing and Publishing Service, Purchase., Software/ Website and Networking, Networking Tools and Accessories, Vehicle and Spare Parts, Spare Parts Sale and Supply
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 29፥ 2012
Deadline :2020-04-22