Pr con

Pr con


የግዥ መለያ ቁጥር Gll 07/8/9/2012 ዓ . ም
ጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲትዩት በ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት ከመንግስት በተመደበለት በጀት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።

1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፣

በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃ /አገልግሎት/ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ከገቢዎች ሚኒስቴር ወይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የድጋፍ ደብዳቤ የሚያቀርቡ፣
የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
2. በጨረታው መሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሎት 1 እና ሎት 2 የማይመለስ ብር 100/ አንድ መቶ ብር/ በ መክፈል ጨረታ ሰነዱን እየከፈላችሁ መውሰድ የምትችሉ ሲሆን፣ በተራ ቁጥር 1፣ 2፣ እና 3 እያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100/ አንድ መቶ ብር/ በመከፈል ጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከተጠቀሰው የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በሥራ ሰዓት ከኢንስቲትዩቱ ቢሮ ቁጥር 119 መውሰድ ይችላሉ::

3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16 ኛው ሎት 1 እና ሎት 2 ጠዋት 4:00 ሰዓት ተዘግቶ 4:30 ይከፈታል:: በተራ ቁጥር 1፣2 እና 3 ከሰዓት 8:00 ተዘግቶ 8:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

4. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዥ የተገለጸውን የገንዘብ መጠን ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ባንክ ጋራንቲ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው::

5. ተጫራቾች የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገቡበትን ፎርማት በመሙላት የተጫራቹን ድርጅት ፊርማና ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው::

6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰንጠረዥ በተጠቀሰው የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በቢሮ ቁጥር 119 በዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ::

7. ጨረታው ከላይ በተገለጸው የመከፈቻ ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንስቲትዩት በግዥና አቅርቦት ቡድን ቢሮ ቁጥር 119 ይከፈታል፡፡

8. የጨረታው መክፈቻ ቀን 16 ኛው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

10. ማንኛውም ተጫራች አሸናፊ በሆነበት ዕቃ ብቃት ማረጋገጫ ካስፈለገ ማቅረብ መቻል አለበት::

11. ስርዝ ድልዝ ያለው እና ማህተም ፊርማ የሌለው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::

12. መ/ቤቱ ባስቀመጠው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዋጋ ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

13. GNSS CORS ኮምፒሊያን ሸት ሞልተው ማቅረብ አለባቸው::

14. ለሎት 1 እና ሎት 2 ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0115543704 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

አድራሻ:- ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አጠገብ

ጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲትዩት



_______________________________
Category : Construction and Construction Machinery, Construction Service and Maintenance, Engineering Service and Equipment, Electro Mechanical Equipment, Printing and Publishing., Printing and Publishing Service

Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 29 ፥2012
Deadline :2020-04-22


Report Page