Pr adv

ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- EFMHACA/FSD/NCB/ADVERTIZING/009/2012
የኢትዮጵያ የምግብ የመድሀኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የማስታወቂያ ስራዎችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ በማወዳደር የአገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በዚህ ጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ በዘርፉ ፈቃድ እና ብቃት ያላቸው ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ህጋዊ ሰነዶች እና በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የ2012 በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌብ ሳይት ላይ የተመዘገቡበት የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ MAT/ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / TIN/ እና Anti bribey pledge form ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤ ቢያንስ እስከ ጨረታው መክፈቻ ዕለት ድረስ የሚያገለግል መሆን የሚኖርበት ሲሆን የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበትን የድጋፍ ደብዳቤ የሚያቀርብ ተጫራች የጨረታው ይሰረዛል ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 150 / አንድ መቶ አምሳ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከባለስልጣን መ/ቤቱ አዲሱ ቢሮ 1ኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው ከግዥና አቅርቦት ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 202 መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ) ሰዓት ድረስ በግዥና አቅርቦት ኬዝ ቲም በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00/ አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ፣ ጥሬ ገንዘብ፣ ባንክ ዋስትና፣ ወይም CPO በFood, Medicine and Healthcare Administration and Control Authority of Ethiopia ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ ኢንሹራንስ ቦንድ ተቀባይነት የለውም፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ ማንበብ አለባቸው፡፡
. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መጀመሪያ ከወጣበት በ16 ኛው ቀን ከቀኑ 8 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8 ፡30 ሰዓት በጨረታ መክፈቻ ስነሥርዓት ላይ ለመገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በባለስልጣን መ/ ቤቱ አዲስ ህንፃ 3 ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበአል ቀን ከሆነ የመክፈቻው ቀን በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን ይሆናል፡
መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 869 74 99 በመደወል መጠየቅ ይቻላል ፡፡
አድራሻ ፦አፍሪካ ጎዳና፣ ቦሌ መንገድ ወሎ ሰፈር አካባቢ
የኢትዮጵያ የምግብ የመድሐኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባስልጣን
_______________________________
Category : Printing and Publishing., Printing and Publishing Service, Public Relations and Advertising, Billboards and Digital Advertising, Public Relations and Public Address Systems
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 25 ፥2012
Deadline :2020-04-18