Pr 70

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04/2012
የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን ለ2012 ዓ.ም ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ እና አላቂ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት፡-
ሎት 1 ልዩ ልዩ የንብረት መመዝገቢያና መቆጣጠሪያ ካርዶች እና የቢዝነስ ካርድ ህትመት ግዥ
ሎት 2 የተሽከርካሪ ጥገና እና ሰርቪስ አገልግሎት ግዥ፣
ሎት 3 የመስክ መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ፣
ሎት4 የIT እቃዎች፣
ማንኛውም ተወዳዳሪ፡-
በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ(ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን፣በመንግስት ግዥ መሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢነት (Supplier list) ምስክር ወረቀት፣ ግብር የከፈለበት ክሊራንስ፣ የጨረታ ተሳታፊነት ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ ብር) ብቻ በመከ ፈል ሰነዱን ከፋይናንስ ቢሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ
ለሎት1 ብር 2000 (ሁለት ሺህ ብር ብቻ) (CPO) ማስያዝ
ለሎት 2 ብር 2000 (ሁለት ሺህ ብር ብቻ) (CPO) ማስያዝ
ለሎት 3 ብር 3750 (ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሀምሳ ብር ብቻ) CPO ማስያዝ
ለሎት 4 ብር 3500 (ሦስት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ) CPO ማስያዝ
3 ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሎት ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጂናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል/ስፔስፊኬሽኑን የያዘውን ሰነድ ኦርጅናሉንና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ አራቱን ፖስታ በአንድ ትልቅ ፖስታ አሽገው ፋ/ግዥ/ን/አስ/ጠ/አገ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
4. በሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ላይ የጨረታማቅረቢያ ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው እራስን ማግለል አይቻልም፡፡
5 አሸናፊው ተጫራች ውል ከመፈፀሙ በፊት ያሸነፈበትን እቃ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ በኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን ስም ማስያዝ አለበት፡፡
6. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በተገለፀለት በ10 ቀናት ውስጥ ውለታ ካልፈፀመ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል፡፡
7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በመጨረሻው ቀን በ4 ፡15 ሰዓት ተዘግቶ 4 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤት አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የጨረታ ሰነድ የመክፈቻው ቀን በዓል ወይንም የእረ ፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይካሄዳል፡፡
8. ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ከሜክሲኮ ወደ ቄራ ወይም ከቄራ ወደ ሜክሲኮ ሲመጡ ቡልጋሪያ ማዞሪያ መስቀለኛ መንገድ ጫፍ ላይ ያሬድ አረጋዊ ህንፃ 3 ኛ ፎቅ ቢቁ 303. ስልክ 011-470-55-83
በኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ
ባለስልጣን የግዥና ንብረት
አስ/ ጠ/ አገል/ ቡድን
Posted date: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 10፥2012
Deadline:May 2, 2020