Pr 68

የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 02/2012
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ በ 2012 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን
ሎት -1 የህከምና እቃና መድሀኒቶች፣
ሎት -2 ቋሚ እቃዎች እና የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች ፣
ሎት- 3 የፅዳት ዕቃዎች ፣
ሎት- 4 የጽህፈት መሳሪያዎች ፣
ሎት -5 የደንብ ልብሶች እና የደንብ ልብስ ስፌት፣
ሎት -6 የህትመት ውጤቶች ፣
ሎት -7 የሕንፃ ቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች ዕድሳት እና ጥገና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፡- በጨረታው መሳተፍ ምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡
በየዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TN NO) ማቅረብ የሚችሉ፣
ተጫራቶች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ከ 50,000.00 በሃምሳ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ (Mat ) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበት እቃ ለሎት1 - 3088/ሦስት ሺ ሰማኒያ ስምንት ብር ብቻ/ ሎት 2-544/አምስት መቶ አርባ አራት ብር ብቻ/ ሎት 3- 190/አንድ መቶ ዘጠና ብር ብቻ ለሎት 4- 1928 /አንድ ሺ ዘጠኝ መቶ ሃያ ስምንት ብር ብቻ ለሎት 5 -1356 /አንድ ሺ ሦስት መቶ ሃምሳ ስድስት ብር ብቻ ለሎት 6 - 1644/አንድ ሺ ስድስት መቶ አርባ አራት ብር ብቻ ሎት 7- 312/ሦስት መቶ አስራ ሁለት ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) በአዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ስም ለማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን ሲፒኦ ያለስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል ።
የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል ውስጥ ያስረከባል ፡፡
ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ብር) በመከፈል በጤና ጣቢያው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር / ተከታታይ የሥራ ቀናት በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነድ ላይ በመሙላት ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 42 ፊት ለፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ቫትን ጨምሮ ዋጋ ሞልቶ፣ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም እና ፊርማ አድርጎ የማይቀርብ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል ::
የጨረታ ሳጥኑ በ10 ኛው ( በአስረኛው ) ቀን ከቀኑ 8 ፡00 ሰዓት ተዘጋጅቶ በዚያው ቀን 8 ፡30 ተጫራቶች ( ህጋዊ ወኪል ) በተገኘበት ወይም ባይገኝም በግልፅ ይከፈታል ::
ተጫራቶች የሚጫረቱበትን አላቂ ዕቃዎች ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ናሙናውን በመስሪያ ቤቱ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 42 በሚገኘው የግዥ ቢሮ ገቢ ማድረግ አለባቸው:: ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ ተጫራች ከውድድሩ ወጪ ይሆናል፡፡ ቋሚ ዕቃዎችን በተመለከተ ደረጃቸውን የሚገልጽ እስፔስፊክሽን ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ::
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
መ/ቤቱ ጨረታውን 20% ጨምሮ ወይም 20% ቀንሶ መግዛት ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 54 60 29/ 01 126 80 48 47 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ ፡- ጉለሌ ክ/ ከተማ አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ጃምቦ ሕንፃ ፊት ለፊት
በጉለሌ ክ/ ከተማ አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ
Posted date: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 11፥2012
Deadline: April 28, 2020