Pr 66

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 014/2012
በደ/ብ/ብ/ሕh/መ/ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ከዚህ በታች የተገለጹትን ህትመቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቶች:-
በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣
በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት(Tin Number) ያላቸው፣
የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸው የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት፣
ማንኛውም ተጫራች የንግድ ፍቃዱን በማቅረብ ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ሀዋሳ በሚገኘው የክልሉ ፋ/ኢኮ/ል/ቢሮ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 304 የማይመለስ 100.00( አንድ መቶ ብር) በመ ክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ ይውላል።
ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸውን ጋዜጣው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው 15 ኛ ቀን ከቀኑ 6 ፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 304 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው አየር ላይ መቆያው ጊዜ ባበቃበት ቀን 6 ፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8 ፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው በጋዜጣ የሚውልበት የመጨረሻ ቀን በዓል፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
ተጫራቾች 20,000( ሃያ ሺህ) ብር የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው።
ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
በተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡- 0462207835/0462126272 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር፡-0462204490/0462211432 መላክ ይችላሉ
በደ/ ብ/ ብ/ ሕ/ ክ/ መ/ ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥና ንብረት
ማስወገድ አገልግሎት/ ሀዋሳ/
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 13፥2012
Deadline: May 5, 2020