Pr 63

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 2/2012
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች እያንዳንዱ ተጫራች እንዲያከብር ይጠይቃል
ከላይ በርዕሱ በመጥቀስ እንደተሞከረው በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ ከተማ ወ/7 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በ2012 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር
ሎት 1/የጽዳት ዕቃዎች
ሎት 2/የደንብ ዕቃዎች
ሎት 3/ አላቂ ዕቃዎች
ሎት 4/ ልዩ ልዩ ዕቃዎች
ሎት5/የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ግዢ
ሎት 6/ፈርኒቸር ዕቃ ግዢ
ሎት 7/የትራንስፖርትና የጭነት አገልግሎት
ሎት 8 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ጥገና
ሎት 9/ የፈርኒቸር ጥገና
ሎት 10/የዲኮር እና የድንኳን ኪራይ
ሎት 11/የመስተንግዶ አገልግሎት
ሎት 12 የህትመት ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
2. በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውንና በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጫረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 / አንድ መቶ ብር ብቻ በመከፈል የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡
4. ወቅታዊ ደብዳቤ በአገር ውስጥ ገቢ ባስስልጣን /tax clearance/ በአቅራቢነታቸው ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ቫት (VAT) ሰርተፍኬትና ቲን (TIN) ሰርተፍኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችል ይሆናል፡፡ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅበታል ::
5. ተጫራቾች በቅድሚያ በባንክ በተ መሰከረለት ሲፒኦ (CPO) የሚጫረቱበት / ሎት 1 / የጽዳት ዕቃዎች ብር 6000 ( ስድስት ሽህ) ሎት 2/ የደንብ ዕቃዎች ብር 7500 ( ሰባት ሺህ አምስት መቶ) ሎት 3/ አላቂ ዕቃዎች ብር 6000 ( ስድት ሺህ) ሎት 4/ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ብር 3000 ( ሶስት ሽህ) ሎት 5/ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ግዢ 10500 አስር ሺህ አምስት መቶ ሎት 6/ የፈርኒቸር ዕቃ ግዢ 4500 ሎት 7/ የትራንስፖርትና የጭነት አገልግሎት ብር 800 ( አንድ ሽህ ስምንት መቶ) ሎት 8/ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ጥገና ብር 2000 ( ሁለት ሺህ) ሎት 9/ የፈርኒቸር ጥገና ብር 3000 ( ሶስት ሺህ) ሎት 10/ የዲኮር እና የድንኳን ኪራይ ብር 1000 ( አንድ ሺህ) ሎት ሀ/ የመስተንግዶ አገልግሎት ብር 500 ( አምስት መቶ) ሎት 2 የህትመት ስራ 500 / አምስት መቶ ብር በቅድሚያማስያዝ ይኖርባቸዋል
6. የመጫረቻ ሰነዱ በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት የጨረታ ማስገቢያ ቦታ ኮ/ቀ/ክ/ ከ/ወ/07 ፋ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
7. ጨረታው 10 ኛው ቀን ላይ ከቀኑ 10 ፡30 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ ጠዋት 4 ፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
8. አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
9. በግዢ አዋጁ መሰረት ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ልዩ አስተያየት ይደረጋል፡፡
10. የአንዱ ዋጋ የማይለወጥ በመሆኑ ተጫራቶች በትክክል መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ እንዲሁም የዕቃው ጥራትና ዋጋ ከግምት በማስገባት አንድትሞሉ፡፡
11. የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢው ወረዳው እስቶር (ዕቃ ግምጃ ቤት) ድረስ አምጥቶ የሚያስረከብ መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ እንዲገባ፤
12. የዕቃውን 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ መ/ቤቱ የሚችል መሆኑን እና ጠቅላላ ዋጋውን 25 ፐርሰንት ለ6 ወር ድረስ ጨምሮ ሊይዝ የሚችል መሆኑን፤
13. ተጫራቹ ለሚወዳደረው ዕቃ ጨረታው ከመከፈቱ ከሶስት ቀን በፊት ለዕቃዎች ሳምፕል (ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
14. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ኮ/ ቀ/ ክ/ ከ / ወ/ 07 ቤቴል እሳት አደጋ ፊት ለፊት በ40 ሜትሩ መንገድ በኩል ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113696634 ይጠቀሙ
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ ከተማ የወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ ቤት
Posted date:አዲስ ዘመን ሚያዝያ 13፥2012
Dead lines: 2020-04-30