Pr 56

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2012
በኮ/ቀ/ክ/ከ ወረዳ 07 ስር የምገኘው ጄ/ዋ/ጉቱ የመጀመሪያ ደረጃ ቁጥር-2 ት/ቤት የተለያዩ ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን ማለትም፡-
ሎት 1 ቋሚ የተገጣጣሚ እቃ፣
ሎት 2 ሕትመት ስራ፣
ሎት 3 የማሽነሪ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል::
ከሎት 1-3 ለተጠቀሱት ዕቃዎች አግባብነት ያለውን የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር መክፈያ ቁጥር ያለቸው እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
የዘመኑን ግብር የከፈሉና በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በአዲስ አበባ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30-11፡30 ሰዓት በኮ/ቀ ክ/ከ ወረዳ 07 በሚገኘው የጀ/ዋ/ጉቱ ቁጥር-2 መ/ደ/ት/ቤ/ት በመገኘት የማይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1 ብር 1000 ( አንድ ሺህ ብር ብቻ) ሎት 2 ብር 125 ( አንድ መቶ ሃያ አምስት ብር ብቻ) ሎት 3 ብር 1350 ( አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሃምሳ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ CPO ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች የሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ አድርገው ማቅረብ አለባቸው:
ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች እያንዳንዱን የሚሸጡበትን ዋጋ እና የጠቅላላውን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመግለፅ በታሸገ ፖስታ ገቢ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውንና የጨረታ ዓይነት በመጥቀስ በጄ/ዋ/ጉቱ ቁ 2 መ/ደ/ት/ቤት ግዥ ክፍል በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
ተጫራቾች ለሚጫረቱት ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃ በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተረጋገጠ በኋላ የውል ማስከበሪያ CPO ማስያዝ አለባቸው።
የሚጻፉ ፅሁፎችን በተመለከተ ተጫራቾች ቦታው ድረስ በመጎኘት ማየት እና መ/ቤቱ በሚሰጠው ዝርዝር አይተው መሙላት አለባቸው።
ጨረታው የሚከፈተው በጋዘጣ ከወጣበት በ11 ኛው ቀን በ4 ፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጄ/ዋ/ጉቱ ቁ 2 መ/ዳ/ት/ቤት ግቢ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል።
ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ: ዓለም ባንክ ወረዳ 7 አለፍ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- 0118346386
በኮ/ ቀ/ ክ/ ከ ወረዳ 07 ጄ/ ዋ/ ጉቱ
የመጀመሪያ ደረጃ ቁጥር-2 ቴ/ ቤት
_______________________________
Category : Machinery., Machinery Spare Parts, Office Supplies and Stationery, Office Items and Equipment, Printing and Publishing., Printing and Publishing Service, Purchase.
Posted Date : አዲስ ዘመን ሰኞ ሚያዝያ 5 ቀን 2012
Deadline :2020-04-22