Pr 55

የጨረታ ማስታወቂያ
ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ ለ 2013 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ አጀንዳዎች እና የጠረጴዛ ካላንደሮች አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል:: ስለሆነም ስራውን ለመስራት ፍላጎቱና ብቃቱ ያላችሁ ድርጅቶች የሚከተሉትን የጨረታ መመሪያዎችን በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
1.ኩባንያው በጨረታ የሚገዛቸው የህትመት ዓይነት የሚከተሉት ናቸው::
1.1 አጀንዳ ............ ብዛት... 3,000
1.2 - የጠረጴዛ ካላንደር ... ብዛት....2,500
2. ተጫራቾች በጨታዉ ለመሳተፍ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው:: እነዚህ ሰነዶች በቴክኒካል ኘሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል::
3. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ከነመመሪያው የማይመለስ ብር 100 ( መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ከኩባንያው ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ ከሚገኘው ሃብት አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ::
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ይሆን ዘንድ የጨረታውን 2 በመቶ (2%) በባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ወይም የባንክ ዋስትና ማረጋገጫ ደብዳበ ይዘው መቅረብ ይገባቸዋል:: የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው በቴኒካል ኘሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል::
5. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳባቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በማለት በግልፅ ከፋፍለው በተለያየ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: የቴክኒካል መወዳደርያ መስፈርቶች በጨረታ ሰነዱ ላይ ይገለፃሉ::
6.ጨረታው ከሚያዚያ 5 ቀን 2012 ዓ.ም እሰከ ሚያዚያ 19 ቀን 2012 ጧት 3 ፡00 ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በእለቱ ( ሰኞ ሚያዝያ 19 ቀን 2012 ዓም ጧት 3 ፡30) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻዉ በተገኙበት ይከፈታል::
7.አሸናፊው ተጫራች ከኩባንያው ጋር የአፈፃፀም ውል ይዋዋላል::
8ኩባንያው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
9.ለተጨማሪ ማብራርያ በስልክ ቁጥር 251-11-558 58 08 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ::
አድራሻ፡ አትላስ አካባቢ የሚገኘው የዓባይ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ. ማ ዋና መ/ ቤት
የሃብት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ቁ. 404 በስልክ ቁጥር 251-11-553 58 08
ዓባይ ኢንሹራንስ ኩባንያ አማ
_______________________________
Category : Printing and Publishing., Printing and Publishing Service
Posted Date : ሪፖርተር እሁድ ሚያዝያ 4 ቀን 2012
Deadline :2020-04-27