Pr 2

የጨረታ ማስታወቂያ 02/2012
በየካ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የካ አባዶ ጤና ጣቢያ የሚያስፈልጉትን
የሠራተኞች ደንብ ልብስ
አላቂ የጽ/መሣሪያዎች
የህትመት ሥራዎች ግዥ፣
የፅዳት እቃዎች፣
ሄቪ ዲዩቲ የልብስ ማጠቢያ ማሽን ባለ 24 ኪ.ግራም ኤግዛሚኔሽን ቤድና መድኃኒትና የመድኃኒት መደርደሪያዎችን፣
ፈርኒቸር፣
የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት በመ/ቤቱ ድረስ መጥቶ ሰፍቶ የማስረከብ በ2012 የበጀት ዓመት ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
በዚህ ጨረታ ላይ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፡
በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል
የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ፕሪንት አውት /ኮፒ/ ማቅረብ የሚችል
የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት /TIN /ያላቸው
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000.00 / ሶስት ሺ ብር / በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ / በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
ዘግይቶ የመጣ ፖስታ ተቀባይነት የለውም፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር / በመክፈል ከጤና ጣቢያው ቢሮ ቁጥር 403 መውሰድ ይችላሉ፡፡
የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት የምትወዳደሩ ተጫራቾች የስፌት አገልግሎት በጤና ጣቢያው ጊቢ ውስጥ ስፌት የምትሰፉ ከሆነ ብቻ ነው መወዳደር የምትችሉት፡፡
ተጫራቾች አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ የተደረጉ ሰነዶች በተለያየ በሰም በታሸገ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከፋይ/ግ/ንብ/አስ/ጠ/አገ/ደ/ የሥራ ሂደት በመግዛት በመውሰድ በጨረታ ሰነዱ ላይ የምትወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ያካተተ ዋጋ በማድረግ ሞልታችሁ በ 11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡ 00 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን ከጠዋቱ 4 ፡ 00 ሰዓት ታላይ ታሽጐ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ በ4 ፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን 11 ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚጥለው ቀናት የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡-ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011893-12-17
አድራሻ፡- የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ስሙ የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም ጊቢ ውስጥ G-7 ብሎክ 306 ጀርባ አካባቢ
በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ ቤት የየካ አባዶ ጤና ጣቢያ
_______________________________
Category : Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Furnitures, Office Furniture, Medical Equipment and Supplies, Pharmaceutical Products/Medicines, Medical/Laboratory Equipment, Office Supplies and Stationery, Stationery Supplies, Printing and Publishing., Printing and Publishing Service, Purchase., Textile and Leather Products, Textiles/ Fabrics and Wearing
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 25 ፥2012
Deadline :2020-04-13