Police

Police


የአዲስ አበባ ፖሊስ የቀሲስ ዐባይ መለሰን ግድያ በተመለከተ " መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ/ም አገልግሎታቸውን ጨርሰው ወደ የሚኖሩበት ሸገር ከተማ ልዩ ቦታው ኤርቱ ሞጆ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመኖሪያ ቤታቸው አካባቢ በተፈጠረ ፀብ ጉዳት ደርሶባቸው በጡሩነሽ ቤጁንግ ሆሰፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው በትላንትናው ዕለት መጋቢት 14 ቀን 2015 ዓ/ም ህይወታቸው አልፏል፡፡ " ብሏል።

" ወንጀሉ በአዲስ አበባ ከተማ ክልል ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ የተፈፀመ እንደሆነና ጉዳዩ ፖለቲካዊ ትርጉም እንዲሰጠው ለማስመሰል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተሰራጩ የሚገኙት መረጃዎች ትክክለኛ አይደሉም " ሲል ገልጿል።

የቀሲስ ዐባይ አስክሬን ለተጨማሪ ምርመራ አቤት ሆስፒታል መላኩን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ቀሪ የፖሊስ ምርመራ እየተካሔደ መሆኑን በሽገር ከተማ አሰተዳደር የፉሪ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ሀላፊ ምክትል ኮማንደር ዳንኤል ኃ/ማርያም ገልፀዋል ብሏል።

@tikvahethiopia

Report Page