Pharmacy

Pharmacy

University information

Pharmacy 


🔖ፋርማሲ ከ other health ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በአድሱ የትምህርት ስርአት freshman course ጨምሮ የ5 አመት ትምህርት ነው ። 


🔖ፋርማሲ ስትገቡ የምትማሯቸው ኮርሶች mostly chemistry ነክ around [ 60%] ,biological around [25%] እና ሌሎችም አሉ ።


🔖ስለዚህ chemistry የሚወድና አንባቢ ተማሪ በብቃት ይወጣዋል። 


   🔬ፋርማሲ ስትማሩ የሚያስደስቱ ነገሮች ፦


🔎 የመድሃኒት ቅመማ በላብላቶሪ ትሰራላችሁ ፤ ከባህላዊ ህክምናና ከእፅዋት እንዴት መድሃኒት ማግኘት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ ፤ በላብላቶሪ ውስጥ lotion, cream, gel, shampoo, sanitaizer....የመሳሰሉትን ኮስሞቲክስ ታመርታላችሁ ፤መድሃኒትን አይጥ ላይ በመውጋት ትመራመራላችሁ ወዘተ....


♦️በፋርማሲ ስትመረቁ ምን ትሰራላችሁ? ገቢውስ እንዴት ነው ? 


1⃣clinical pharmacy የሚባለው እ hospital ውስጥ ተቀጥራችሁ 


2⃣pharmaceutical company የመድሃኒት ፋብሪካና በተወሰነ መልኩ የኮስሞቲክስ ፋብሪካ ጋር


3⃣የመድሃኒትና የምግብ ቁጥጥር ማለትም ወደ ሀገር የሚገቡና የሚወጡትን መፈተሽ


5⃣በግላችሁ community pharmacy በመክፈት በተለይ ቤተሰቦቻችሁ በገንዘብ የሚያግዟችሁ ከሆነ በጣም አዋጭ ነው።


6⃣የማንኛውንም የህክምና መድሃኒትና ቁሳቁስ በ pharmacist ቁጥጥር ስር ነው የሚገዛው (የሚቀርበው) ስለዚህ እዛ ላይም የናንተ ሙያ አለ።


7⃣የ fingerprint,forensics, food toxicity,drug toxicity,.....የመሳሰሉትን የወንጀል ምርመራ ላይ መስራት ይቻላል ።


8⃣እኛ ሀገር ብዙም ባይኖር የመድሃኒት ጥናትና ምርምር ላይም ትሰራላችሁ


✅ስለ ገቢው፦ እውነቱን ለመናገር በፋርማሲ ትምህርት ከተመረቃችሁ በኋላ ስለ ገንዘብ አያሳስባችሁም ። እያጋነንኩ አይደለም ከቻላችሁበት በጣም ባለሀብት ትሆናላችሁ ። ስለ ፋርማሲ ብትጠይቁ ቀድመው የሚነግሯችሁ business ነውና እሱ አያሳስባችሁ ።


✅ስራ ላላገኝ እችላለሁ? እንደማንኛውም የጤና ተማሪ ከhospital,ጤና ጣቢያ ትሰራላችሁ plus ሌላ አማራጭ በግል ትሰራላችሁ ወይም ከላይ ከ ተራ ቁጥር 2-7 ያሉት አማራጮች አሉላችሁ ። 


📗ትምህርቱ ከባድ ወይስ ቀላል? pharmacy ከ medicine በመቀጠል የሚመደብ ስለሆነ ከበድ ይላል ነገር ግን chemistry,biology and labolatory ነክ ትምህርቶች ለሚሰራና ለሚያነብ ተማሪ በቀላሉ ማለፍ ይችላል ። እንደዬ ዩንቨርስቲው ቀለል ባለ መልኩ የሚያስተምሩም አሉ ። ስለዚህ ጠንከር ያለ ተማሪ ቢሆን የተሻለ ውጤት ያመጣል።


⭕️በአጠቃላይ ፋርማሲ ከሌሎች የጤና ዘርፎች ለየት የሚያደርገው ብዙ የስራ መስኮች ያሉትና ጥሩ የሚባል ክፍያ የሚገኝበት መሆኑ ነው። 


⭕️ስለ ፊልድ መረጣ በተመለከተ እንደ medicine ገና የመጀመሪያ ሴሜስተር ኮርስ እንደጨረሳችሁ ነው ። ሌሎች other health ግን 1ኛ አመት ከጨረሳችሁ በኋላ ነው።


https://t.me/Campus_Info_bot

https://t.me/Campus_Info_bot

Report Page