PR,comp
አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 002/2012
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የሚከተለውን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት አንድ፡- ዴስክቶፕ ኮምፒዩተር፣ ላፕቶፕ እና ተያያዥ ዕቃዎች
- ሎት ሁለት - የህትመት እና ተያያዥ አገልግሎቶች
በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ሟሟላት ይጠበቅባቸዋል ።
- ተጫራቶች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ኦዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት እቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የቴክኒከ ፕሮፖዛል “አንድ ኦርጅናል ኮፒ” እና የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር እንድ ኦርጅናል ኮፒ” የድርጅቱ ስም፣ አድራሻ እና ማህተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት ሎት በመፃፍ እና በየሎቱ በመለየት በታሸገ በኤንቨሎፕ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 11:00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን (በሚቀጥለው የሥራ ቀን) ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 2012 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ጠቅላላ ከሚወዳደሩበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ለሎት እንድ 2%፣ ለሎት ሁለት 2% በሚወዳደሩበት ሉት ሰባንክ በተመሰከረለት ቼክ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር እያይዘው ማቅረብ እለባቸው። CPO መስራት ያለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በሚል አድራሻ መሆን አለበት።
- ተጫራቶች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6:00 ሰዓት ጨምሮ ለሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊትለፊት አማጋ ሕንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አስተዳደር ቡድን በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተፈታ (ቫት) ጨምሮ ወይም ተፈታ (ቫት) በፊት መሆኑን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል። ያልተገለፁ ከሆነ ተእታ (ቫት) ጨምሮ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቶች በጨረታው ሰነዱ የተገለፀው የመምጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በጨረታው ሰነዱ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውለታ ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
- ተጫራቶች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም ዕቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት ናሙናዎችን ለግዥ አስተዳደር ቡድን ማስገባት አለባቸው።
- አሸናፊ ተጫራቶች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ለጨረታ ከቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጵ/ቤት እሰከ 20% (ሃያ ፐርሰንት) ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በተጨማሪ መረጃ
- በስልክ ቁጥር፡- 0115-57-57-42/0115-57-57-19 በመደወል ወይንም ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት አማጋ ሕንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አስተዳደር ቡድን በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የገቢዎች ባስሥልጣን
Posted date:አዲስ ዘመን መጋቢት 12፣ 2012
Dead line:March 31,2020(መጋቢት 22)