PM Abiy Ahmed

PM Abiy Ahmed


ድርድርን በተመለከተ

ከለውጡ በኋላ በውጪ የሚገኙ ተፎካካሪ አካላት እንዲገቡ ተደርጓል። ከምርጫም በኋላ ከአሸናፊው ፓርቲ ውጪ በመንግሥት ስርዓት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርጓል። በጋራ ሀገር መገንባት መልካም ነገር ነው። ችግሩ ጽንፈኝነት እና ጥላቻ ነው። ባለፉት ከ40 የሚበል ጡዓመታት ሕወሃት ትግራይን አስተዳድሯል። ግን ያኔ የነበረው ችግር አሁንም አለ። ለትግራይ ሕዝብ ምንም አልተረፈውም። ፓርቲ ሲኮን ለሕዝባችን ምን ዋጋ እንጨምራለን የሚለው ታሳቢ መደረግ አለበት። በውጊያ አትፈርስም ብለን ሀገር እንዳስቀጠልን፣ በልማት ደግሞ ተግተን እንቀጥላለን ።ለልጆቻችን ቁርሾ ሳንተው፣ እኛ ዋጥ አድርገን ለልጆቻችን ሰላምን እናውርስ። ከማንም ጋር ሰላም ነው የምንፈልገው። እያንዳንዷ የሰላም ቀን ለእኛ ትርፍ ታስገኝልናለች። ሕዝብ ሳያውቀው የሚደረግ ድርድር የለም። በይፋ የታወቀ አጥኚ ኮሚቴ ተቋቁሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካኝነት እየተመራ ሲሆን፣ እስካሁን ውጤቱን አላሳወቀም። የሚደራደረው ኮሚቴም ይሄ ነው። ውጊያ ሲመጣ ለሕዝብ አሳውቀን የጀመርን ሰዎች፣ ድርድር ከተጀመረ የሚያስደብቀን የለም። ነገር ግን፣ የብቻ ጠላት የለም የሀገር ጠላት እንጂ፣ ለብቻም የሚሰራ ሥራ የለም በጋራ እንጂ። የእኛም የሕዝባችንም ፍላጎት ለጥይት የሚወጣ ውጪ ለልማት እንዲወጣ ነው። ሰላም እንፈልጋለን ማለታችን የተደበቀ ድርድር እናደርጋለን ማለት አይደለም። 


የጸጥታ ተቋማት ዝግጅት


የጸጥታ ተቋማችን የሚዘጋጀው ለሕወሓት አይደለም። የኢትዮጵያን ሕልውና ለማስቀጠል ነው ።ብዙ ሥራ ይጠበቅብናል፣ ነገር ግን በቂ አይደለም። በቁጥር፣ በብቃትና በዕውቀት እያደገ መሄድ አለበት። ዝግጅቱ ደግሞ አካላዊ ብቻ ሳይሆን የሳይበርም ጭምር ነው። ዘንድሮ በእኛ ላይ 5860 በአኢንተርኔት የታገዘ ጥቃት ተደርጓል። በሚሊየን የሚቆጠሩ ብሮች ያጣንበት አለ፣ በቢሊየኖች ያተረፍንበትም አለ። በልዩ ልዩ መንገድ የጥቃት ሙከራ ይደረግብናል። ዝግጅቱ በዚህም አንጻር ነው። ለድርድሩ የግል ጥቅም ብቻ ሳይሆን የሀገር ትርፍ መታሰብ አለበት። በድርድር ሰላም ከመጣ አንደኛ ተጠቃሚ የሚሆነው የትግራይ ሕዝብ ነው። በዚህ ጦርነት የሚነግዱን ሁሉ የሚያሳርፍም መፍትሔ ይሆናል። እኛ ለሰላም መትጋታችንን አናቋርጥም ግን የምናገኘው መልስ በዚያው ያክል ይሆናል ማለት አይደለም። 


የሕግ ማስከበርን በተመለከተ


በብልጽግና በኩል በሕዝቡን ፍላጎት ለማድመጥ ስንሞክር ሰላም፣ የኑሮ ውድነት እና መልካም አስተዳደር ዋነኛ ጥያቄዎች ሆነው ተነስተዋል። ከሁለት ወር በትፊ በብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ ተሰብስበን፣ ጉዳዮችን ለይተን አውጥተናል። በዚህም በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል የጸጥታ ሁኔታ፣ በአዲስ አበባ (ቅሚያ እና የጠላት ቅጥረኞች) እንዲሁም በሶማሌ ደግሞ አልሸባብና ኮንትሮባንድ ዋነኛ የሰላም እክል ሆነው ተገኝተዋል። ከበ2 ወራት ውስጥ 1000 የሚበልጡ የሸኔ አባላት ርምጃ ተወስዶባቸዋል። በተሰራው የሰላም ማስከበር ሥራ በሁሉም ስፍራዎች መልካም ውጤት አግኝተናል። ከዚያ በኋላ መልሰን ሕዝቡን ስናወያይ መልካም ምላሽን አግኝተናል። ርምጃዎች ሲወሰዱ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለማስለመድ በተቻለ መጠን ሰላማዊ አማራጮችን ለመከተል ተሞክሯል። ይህም መንግሥትን አቅመ ቢስ አስመስሎታል። ነገር ግን፣ ኃይልን የመጠቀም ስልጣን ያለው መንግሥት እንደ ሆነ መታወቅ አለበት። 


በአማራ ክልል በተወሰደው ርምጃ የፌደራል መንግሥት ሳይሆን፣ የክልሉ ልዩ ኃይል ነው የተሳተፈው። የየክልሉን የሕግ ማስከበር ዘመቻ የሚመራው የክልሉ ኃይል ነው፣ ከፌደራል የሚያገኘው የቴክኒክ ድጋፍ ብቻ ነው። ርምጃው አካባቢያዊ መሆኑን፣ በሕዝብ ጥያቄ እንደ ተጀመረ፣ በተገኘው ውጤት ሕዝብ ደስተኛ መሆኑን እና ሰላም እያገኘ መሆኑ መታወቅ አለበት። በሀገር ወዳዶች ስም የሚቆሙ አጥፊዎችን ለሕግ ማቅረብ ግዴታ ነው። በክልሉ በሕግ ማስከበር ርምጃ 3500 የከዳ ሰራዊት ተይዟል፣ ከዚሁም ውስጥ ከ2000 የሚበልጠው ከልዩ ኃይል የወጣ ነው። ሃሺሽ፣ የውጪ ምንዛሬ፣ ተቀጣጣይ ፈንጂ እና ቦንብ ይዘናል። ከዘመቻው በኋላ የገባ እና መከላከያ ብቻ የሚታጠቀው አዲስ አይነት ጠመንጃ አለን። መከላከያን ገድለው ያንን ጠመንጃ ታጥቀው የተገኙ ሰዎች ናቸው የተያዙት። እሳት ቤት እንዳያጠፋ ሰብሰብ ተደርጎ መያዝ አለበት። ነጻነትና ብልጽግና የሚኖረው ከመረጋጋት ጋር ነው።

በስህተት የተያዘ፣ ያለአግባብ የተጎዳ ሰው ሊኖር ይችላል። ተጣርቶ የእርምት ርምጃ ሊወሰድ ያስፈልጋል። 


የ‘ተረኝነት’ ጉዳይን በተመለከት


ሀገራችን ለሁላችንም የሚበቃ ሀብት አላት። የተፈጥሮ፣ የታሪክ፣ የባህል እና ከምንም በላይ የጊዜ ሀብት አለን። ይህን ሰብስቦ ለጥቅም ማዋል ሲቻል፣ ሀገርን እንደ እቁብ አይቶ በዚህኛው ቀን ለእከሌ፣ በሌላ ቀን ለእከሌ በፈረቃ የምትደርስ ያደርጋታል። እንኳን ለሀገር፣ ለመብራትም ፈረቃ ይከብዳል። ሀገር የምትመራው በጋራ ነው። ሕግ አውጪ፣ ሕግ ተርጓም፣ ሕግ አስፈጻሚ እና ርዕሰ ብሔር የሀገረ መንግሥቱ ምሰሶዎች ናቸው። 


በሲቪል ሰርቪስ በተደረገው ቆጠራ አማካኝነት በመንግሥት አስተዳደር የብሔር ተዋጽኦ ሁሉን አቀፍ መሆኑን፣ በፌደራል ሠራተኞች ደረጃም ጭምር አይተናል። የልማት ድርጅቶችም ተፈትሸዋል። ለምሳሌ፦ አየር መንገድ የሥራ አስፈጻሚው 74 በመቶ አማራ፣ 5 በመቶ ትግሬ፣ 5 በመቶ ኦሮሞ ቀሪውን የተለያዩ ብሄሮች የተውጣጡበት ነው። አየር መንገዱ በውጪም ያካተተው አስፈጻሚ 52 በመቶ አማራ፣ 16 በመቶ ኦሮሞ፣ 15 በመቶ ትግሬ ቀሪውን የተለያዩ ብሄሮች የተውጣጡበት ነው።


ምክር ቤቱ ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ወስዶ የብሔር፣ የጾታ፣ የእምነት እና የመሳሰለውን ተዋጽዖን የተመለከተ ሕግ አውጥቶ በዚያ መሠረት ቢያስፈጽም የሚነሳውን ጥያቄ ሁሉ በሚገባ ይቀርፈዋል።

የምናነሳው ሀሳብ ሁሉ በእውነታ እንጂ በተረት ላይ የተመሰረት አይሁን።


ሁሉን አካታች ብሄራዊ ምክክርን በተመለከተ


የምክክር ኮሚሽኑ በምክር ቤቱ አማካኝነት ተቋቁሞ ብቁ ናቸው የሚባሉ ሰዎች እንዲያንቀሳቅሱት ተመርጠዋል። ገና ከጅምሩ እየተቸን ካላበረታታናቸው ውጤታማ ሊሆኑ አይችሉም። ክርክር ሳይሆን ምክክር አድርገው ወደ ጠቃሚ አቅጣጫ እንዲያመላክቱ ድጋፍ ሊደረግላቸው ያስፈልጋል። ምክር ቤቱ፣ መንግሥት፣ ፓርቲዎች አግዘው ምክክሩ ወደ ጫፍ ቢደርስ ሀገርን ይጠቅማል ብዬ አምናለሁ።


ሌብነትን በተመለከተ፡- በሌብነት ዳኞች፣ አቃቤ ሕግ፣ ፖሊስ፣ አኦዲተር፣ ሌብነትን ለማጥፋት የተዘጋጁ አካላት ይገኙበታል። የውስጥ ተሀድሶ እናደርግበታለን። ቤተ እምነቶችም ጋ ሌብነት አለ። በስነ ስርዓቱ ግለሰቦች ኦዲት ተደርገው ቤተ እምነቶቹ ተጠቃሚ ሊሆኑ ያስፈልጋል።


ወርቃማውን አማካይ ፍለጋ፦ ዴሞክራሲያዊ መብትና ሰላምና ጸጥታን ማመጣጠን፣ የብሔር እና የሀገር ጉዳይን ሳይቀላቅሉ፣ ሳያዋውጡ ማመጣጠን፣ የግለሰቦች መብት እና የቡድን መብትን ማመጣጠን ያስፈልጋል፣ የትናንትና ታሪክና የትናንትና ፈተናን ማመጣጠን፣ ብሄራዊ ጥቅም እና የዓለም አቀፍ ግንኙነትን ማመጣጠን እና ወርቃማውን አማካይ መፈለግ ያሻል።


የሞራል ዝቅጠትን ማስወገድ አለብን።


ልማትን የሚያደናቅፍ፣ አንድነትን የሚያደናቅፍ፣ የሀገር ጥቅምን የሚያጎድል ያልተገባ የውጪ ጫናንም መገዳደር አለብን።


ተሻጋሪ ተቋማት፦ ተቋማት በመርህ ላይ ተገንበተው ጊዜን ተሻጋሪ መሆን አለባቸው


ልማት ጠል እና ሥራ ጠል አስተሳሰብን ማስወገድ አለብን።


#የጠሚሩምላሾች

#PMAbiyresponds

Report Page