Others sale textile 13

Others sale textile 13


እስከ ግንቦት 17 /2012 አ.ም ብቻ የሚቆይ ልዩ ቅናሽ! በ 0919415260 አሁኑኑ ይደውሉ በርካታ የክፍያ አማራጮች አመቻችተንልዎታል!

የጨረታ ቁጥር 04/2012 ዓ. ም

በጉለሌ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ደጋፊ የሥራ ሂደት የ2012 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የተለያዩ ችግኞች አና የደንብ ልብስ ስፌት ግዥ አንፀባራቂ ልብስ ጨረታ ከላይ የተገለጸውን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከላይ በርዕሱ የተጠቀሰውን የተለያዩችግኝ እና የደንብ ልብስ ስፌት ግዥ እና አንጸባራቂ ልብስ ግዥ በግልጽ ጨረታ መወዳደር ይችላሉ::

ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና በዘርፍ የተደራጀና የተመዘገቡ።
የግብር ከፋይነት (tin number) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND) ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ማለትም የተለያዩ ችግኝ 5,000 ብር 2 የደንብ ልብስ ስፌት 2,000 ብር 3. የአንጸባራቂልብስ 5,000 ብር የባንክ ጋራንት ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ለ60 ቀናት የሚያገለግል ሆኖ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት::
ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመሰሰ የጨረታ ሰነድ ብር 100.00( አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በo (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታው ሰነድ ዘወትር በሥራ ቀን በጉለሌ ክፍለ ከተማ አዲሱ ገበያ ኖክ ማደያ ጀርባ ያለው አዲሱ ሕንፃ ውስጥ አንደኛ ፎቅ የግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያውን ዋጋ ከመሙላት እና የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በሁለት(2) ኮፒ በፖስታ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት 10 ኛው ቀን እስከ 8:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
ጨረታው 10 ኛው ቀን ከሰዓት 8 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
የጨረታው አሸናፊ ለመልካም አፈጻጸም (ለውል ማስከበሪያ ) ያቀረቡትን ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ዝርዝር (Specification) መሠረት የሚያቀርባቸውን ችግኞች እና ሳምፕል ማቅረብ አለበት፡፡
አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ከተገለጸበት ከ7 የሥራ ቀናት በኋላ በ8ኛው የሥራ ቀን ውል መፈጸም እና ውል ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ ለችግኞች እና ለአንጸባራቂ ልብስ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ግዥ ለፈጸመው መሥሪያ ቤት ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት።ለደንብ ልብስ ስፌት 5 ቀን ውስጥ አጠናቅቆ ማቅረብ አለበት::
መ/ቤቱ የአሸነፉትን ዕቃ ከውል በፊት 20 ፐርሰንት ከውል በኋላ 25 ፐርሰንት የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የተሞላው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት ካልተካተተ እንደተካተተ ተደርጎ ይያዛል፡፡
ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ በስልክ ቁጥር፡- 011-8-12-41-58 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርጉለሌ ክ/ ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ደጋፊ የሥራ ሂደት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 11 ቀን 2012
Deadline: May 29, 2020


© walia tender

Report Page