Other total ethiopia 1

Other total ethiopia 1


ቶታል ኢትዮጵያ በነቀምት ከተማ የሚገኘውን የነቀምት ቡና ቦርድ ነዳጅ ማደያ ለግለሰብ ኦፕሬተር የሽያጭ ወኪልአወዳድሮ ለተወሠነ ጊዜ በውል መስጠት ይፈልጋል፡፡

መወዳደር የሚፈልጉ አመልካች ግስሰቦች፤

በትምህርት ደረጃቸው ቢያንስ 10ኛ ክፍልን ያጠናቀቁና የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
የነዳጅ ማደያው ሥራ የሚጠይቀውን የመሥሪያ ካፒታል /ገንዘብ/ በግላቸው የማቅረብ አቅም ያላቸው፣
. ወቅታዊ የሆነና ያለፉትን 6 ወራት የሚያሳይ በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ስቴትመንት ማቅረብ የሚችሉ ሆነው ከባንኩ የማረጋገጫ ደብዳቤ ማምጣት የሚችሉ፣
የነዳጅ ማደያውን የዕለት ተዕለት ሥራ በቂ ጊዜ ሰጥተው በግላቸው ማንቀሳቀስ የሚችሉና፣ የስራ በልምድ ማቅረብ የሚችሉ፣
አመልካቾች የነቀምት ከተማ ወይንም አካባቢ ነዋሪ ቢሆኑ ይመረጣል፣
ጊዜው ያላለፈበትና ተቀባይነት ያለው መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሱ ግለሰቦች፤

. የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የማመልከቻ ሰነዱን ሙለጌ ህንፃ ሰባተኛ ፎቅ በሚገኘው ዋና መ/ቤታችን የሽያጭ ቢሮ ድረስ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት መጀመሪያ ቀን ከግንቦት 09 ቀን 2012 ዓም እስከ ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ. ም. ከቀኑ 10 ፡00 / አስር ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ዝተውና ሞልተው መመለስ ይኖርባቸዋል።
ከላይ ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ በኋላ የሚቀርብ የማመልከቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ውድድሩን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ከማመልከቻ ሰነድዎ ጋር የሚከተሉት ደጋፊ መረጃዎች አባሪ መደረጋቸውን አይዘንጉ፤

የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ፎቶ ኮፒ፣
ያለዎትን እና ለስራው የሚመድቡትን የገንዘብ አቅም ለማሳየት እንዲቻል ወቅታዊ የሆነ ቢያንስ የ6ወር ተቀማጭ ተንቀሳቃሽ ሂሳብዎን የሚገልጽ የባንክ እስቴትመንትና የባንክ የማረጋገጫ ደብዳቤ፣
የትምህርት ደረጃዎን የሚያሳይ የተሟላ የትምህርት መረጃ ፎቶ ኮፒ፣
ያለዎትን ንብረት የገንዘብ አቅም ለማሳየት እንዲቻል ወቅታዊ የሆነ የቋሚ የንብረት ባለቤትነት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ /ካለ/
ቶታል በዓለም አቀፍ ደረጃ አንጋፋ ከሆኑትና በነዳጅ፣ በተፈጥሮ ጋዝ እና በዝቅተኛ ካርቦን ኤሌክትሪሲቲ ሽያጭ ላይ የተሰማራ ኩባንያ ሲሆን በዓለማችን በ30 አገራት ላይ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ቶታል በኢትዮጵያ ውስጥ ኢኤ.ኢ ከ1950 ዓ.ም. ጀምሮ አገልግሎት ላይ ያለ ሲሆን፡ ከ10 ዓመት በፊትም ከሞቢል ኢስት አፍሪካ ጋር ውህደት ፈፅሞ በጠቅላላው በመላው ሀገሪቱ ከ150 በላይ በሆነ ነዳጅ ማደያዎችና 5 የነዳጅ ማከማቻ ዴፖዎች ሃላፊነት በተሞላው መንገድ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ቶታል ኢትዮጵያ ኢማ. በሀገሪቱ ካሉት የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች ግንባር ቀደሙ ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ

በስልክ ቁጥሮች፡ - 011 465 11 25 011 465 45 25 emlt: www.total.com www.totalethiopia.com ድሕረ ገፆቻችንን ይጎብኙ፡፡

ቶታል ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 09 ቀን 2012
Deadline: May 26, 2020


© walia tender

Report Page