Other car 8 aau

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር : AAU/NCB/VER/29/12/20
የተለያዩ መኪኖች ኪራይ አገልግሎት ግዥ ጨረታ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ መኪኖች የኪራይ አገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተጠቀሰውን የተለያዩ መኪኖች የኪራይ አገልግሎት ግዥ ለማቅረብ ብቃት ያላችሁ ድርጅቶች በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነድ እንድታቀርቡ ተጋብዛችኋል።
ጨረታው የሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት የመንግስት ግዥ አዋጅ በተገለጸው ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ሥነ-ስርዓት መሰረት ይፈጸማል። የተለያዩ መኪኖች የኪራይ አገልግሎት ግዥ ጨረታ የሚከናወነው ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች እና ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ በ2012 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፤ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽ ወቅታዊ ደብዳቤ ከአገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን፤ በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ዌብሳይት ላይ ፕሪንት አድርጋችሁ፤ ቫት እንዲሁም ቲን ሰርተፍኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችል ይሆናል:: ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ በማጻፍና በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን በነጻ መውሰድ ይችላሉ።
የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 6(ለ) በተገለጸው አድራሻ ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ. ም እስከ 4 ፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። የጨረታ ማስከበሪያው በተጫራቾች መመሪያ በተዘረዘረው መሰረት አያይዘው ያቀርባሉ። ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም። በጨረታው ላይ ለመገኘት የፈለጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቁጥር 6 (ሐ) በተጠቀሰው አድራሻ ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ. ም ከጠዋቱ 4 ፡30 ይከፈታል።
ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራቁጥር 6 (ለ) በተገለጸው አድራሻ ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ. ም እስከ 4 ፡00 ሰዓት ወይም በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት (በግዥ ክፍል ከጨረታ መክፈቻ ጊዜ በፊት በማቅረብ ይሆናል)። ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር 20,000.00 ( ሃያ ሺ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
ሀ/ ሰነዶቹን የሚወስዱበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 312.
ለ/ የጨረታ ሰነድ የሚገባበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 200.
ሐ/ ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 200.
የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት 2:00-6:00 እና 8፡00-11፡00 ብር 300 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ። ፡
ድርጅታችን በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው።
ስልክ ቁጥር፦011-12432-72/011-12490-30
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ የግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 07 ቀን 2012
Deadline: June 2, 2020
© walia tender