Other AA police comition 2

Other AA police comition 2


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር AAPC NCB007/2012 ዓ/ ም

የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በ2012 በጀት ዓመት ለኮሚሽኑ ለፖሊስ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን፡

ስስዚህ፡- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አስባችው፡፡

በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን እና በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ይመልከቱ የሚል ፅሑፍ በግልጽ ማቅረብ አለባቸው፡፡
የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ፡፡
ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ እና የታደሠ ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው
የመንግሥት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤
አማራጭ ዋጋ እና አማራጭ ዕቃ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም፡፡

በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቶች ቴክኒካል ሰነዶችንና የዋጋ ማቅረቢያዎች ፋይናንሻል/ሰነዶች በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለባቸው፡፡.
ማንኛውንም ተጫራቾች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበትን ዕቃ ዓይነት በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን፤ ስረዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲፒኢ ከቴክኒክ ሰነዶችጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡
በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አአበባ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ግምጃ ቤት ወይም በክፍል 6 በፍላጎት መግለጫው በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው፡፡
በጨረታ ሰነድ በክፍል 6 ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ በሚገለጸው መሰረት ጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው መሰረት ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡
. ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙናም ሆነ አሸናፊ መሆናቸው ሲረጋገጥ ያቀርቧቸው ዕቃዎች ኮሚሽኑ ባወጣውፍላጎት መግለጫ /sepecification/ መሰረት መሆኑን በኮሚሽኑ የጥራት ኮሚቴ ወይም በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ኤጀንሲ አማካኝነት የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
. ናሙናው ገቢ መሆን ያለበት ጨረታው በሚከፈትበት ቀን እስከ 4፡00 ድረስ ገቢ መሆን አለበት፡፡
ተጫራቾች አራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢ ጽ/ ቤት ቢሮ ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሙግዛት ይችላሉ፣
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በ11ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በኮሚሽኑ ግዥና ፋይናንስ 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

በጨረታ ሰነዱ ክፍል 2 ላይ በሚጠቀሰው ቀን ጠዋት 4 ፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4 ፡30 ሰዓት ሲሆን በመ/ ቤቱ 5 ኛ ፎቅ ትንሹ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 512 ይከፈታል፣
የጨረታው መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው 4 ፡00 ሰዓት ታሽጎ 4 ፡30 ሲሆን ይከፈታል፡፡
ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡


ለበለጠ መረጃ በስ/ቁጥር፡- 0111 11 04 48 /011-8-33-32-57


የአ/ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን


Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 21 ቀን 2012

Deadline: June 8, 2020


© walia tender

Report Page