NCDs & Mental Health
Crohn’s & Colitis Ethiopia
ስር የሰደዱ ህመሞችና የአእምሮ ጤና
የተለያዩ ስር የሰደዱ ህመሞች ጭንቀት፣ ስጋት እና ድባቴን በመፍጠር በአንድ ሰው ህይወት ላይ እክልን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ የእነዚህ የህመም ስሜቶች በስራ፣ በትምህርት፣በግንኙነት፣በመጓጓዝ እና በአካላዊ እና ስሜታዊ ጤንነት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ፡፡
በሌላ በኩል ፣ የአእምሮ ጭንቀት ሁኔታ ሲከሰት የተለያዩ የስር የሰደዱ ህመሞች ምልክቶች እና የህመሞቹን መልሶ መቀስቀስ ሊያስከትል ይችላል፡፡ የስር የሰደዱ ህመሞች መልሶ መቀስቀስ የሰውነት የመቆጣት መጠን በመጨመሩ ምክንያት የሚከሰት ብቻ ሳይሆን፤ በአእምሮ ጭንቀቱ ወይም በስሜት መረበሽ ምክንያት የሰውነት ህመሙን የመከላከል አቅም ከመቀነስም ጋር ይያያዛል፡፡
ከላይ ከተጠቀሱት የቱም ይቅደም የቱ፣ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ጭንቀት፣ ስጋት እና ድባቴ በቀጥታ ስር የሰደዱ ህመሞችን ላያስከትሉ ቢችሉም ቀድሞ ለተፈጠረው ህመም አፀፋዊ ምላሽ ናቸው፡፡
ስር ከሰደዱ ህመሞች ጋር ተያይዘው የሚጠቀሱ ስሜታዊ ምላሾች
ከጭንቀት፣ ስጋት እና ድባቴ በተጨማሪ ስር የሰደዱ ህመሞች ያለባቸው ሰዎች ሌሎች ተጨማሪ የስሜት ለውጦችን ሊያስተናግዱ ይችላሉ፡፡ እነዚህም፡
✔️ህመሙ እንዲከሰትባችው ያጠፉት ጥፋት እንዳለ በማሰብ የጥፋተኝነት ስሜት መሰማት
✔️ህይወታቸውን ለመቀጠል በሌሎች ላይ መደገፍ እንዳለባቸው መሰማት፤ በራሳቸው ለመቆም አለመቻልን ማሰብ
✔️ያለመታመን ስሜት ( ዕቅዶችን መሰረዝ፣ በህመም ምክንያት ከስራ ቦታ መቅረት….) በዚህም ምክንያት ሌሎችን የመጉዳት እና ስራን የመበደል ስሜት
✔️ስለ ጤና ሁኔታቸው ለሰዎች ለመናገር የእፍረት ስሜት መሰማት
✔️ያጋጠማቸውን ህመም ያለመቀበል እና መካድ፣ በዚህም ምክንያት ላጋጠማቸው ህመም ተገቢውን ጥንቃቄ አለማድረግ
መፍትሔዎችና ተግባሪያዊ ማሳያዎች
👉ያጋጠመንን ህመም መቀበል የለት ተዕለት ኑሯችንን በተገቢው ሁኔታ ለማስኬድ፣ የሀኪማችንን ምክር በአግባቡ ተቀብሎ ለመፈፀም እና ጤናማ ህይወት ለመኖር ይረዳናል፡፡ስር ከሰደዱ ህመሞች ጋር ስንኖር በተለያዩ የስሜት ለውጦች ውስጥ ማለፍ የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን ህመማችን ስለእኛ ሊያብራራ እንዲሁም እኛን ሊገድበን አይችልም፡፡ለእኛ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች እንዲሁም የምንወዳቸውን ነገሮች መስራት መቀጠል አለብን፡፡መለወጥ የምንችለውን ነገር መለወጥ እንዲሁም መለወጥ የማንችለውን መቀበል አለብን፡፡ለራሳችን ተገቢውን እንክብካቤ መስጠት፤ከጓደኛ፣ ከቤተሰብ እና ከጤና ባለሙያዎች ጋር በመሆን ተገቢውን የህክምና ሂደት ሁሉ በማድረግ ህመሙን መቆጣጠር እና መከታተልን መማር አለብን፡፡
የአእምሮ ጤናን ለመጠበቅ በየዕለቱ ማድረግ ከምንችላቸው ተግባራዊ ማሳያዎች ውስጥ:
✅️ከሰዎች ጋር መገናኘታችንን ማረጋገጥ
✅️ለምንፈልገው ነገር መሰጠት
✅️ተዝናኖት
✅️የምናመሰግንባቸውን ነገሮች መፈለግና ማጉላት
✅️በአካላዊ ሁኔታ ንቁ መሆን
✅️ከተገቢው በላይ ነገሮችን ከማጉላትና ስሜታዊ ከሆነ አስተሳሰብ መራቅ
✅️ለህመሙ መከሰት የጥፋተኝነት ስሜት፣ ግላዊነት ማላበስና ራስን መውቀስን ማቆም
በተጨማሪም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ራሳችንን በመጠየቅ ጥሩ የሆነ የአእምሮ ጤና እቅድ ሊኖረን ይችላል፡፡
ጤናዬን ለመጠበቅ በየዕለቱ ማድረግ ያለብኝ ነገሮች-
❔️በየዕለቱ የማስታውሳቸውን ጥሩ ስሜትን የሚፈጥሩልኝ ነገሮች ምንድን ናቸው?
❔️በተግባር ላይ ለማዋል ማሰብ ያለብኝ ነገሮች- በየእለቱ የማላደርጋቸው ነገር ግን በየእለቱ ለማድረግ እቅዴ ውስጥ ማስገባት ያሉብኝ ነገሮች ምንድን ናቸው?
❔️ማድረግ የሌሉብኝ ነገሮች - በከባድ የስሜት ለውጥ ውስጥ ሳልፍ ጠቃሚ ያልሆኑ የማደርጋቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?
❔️የቅድመ ማስጠንቀቂያ ምልክቶችን ማወቅ - ከፍ ካለ የስሜት መቃወስ በፊት ያስተናገድኩዋቸው እና ትኩረት ልሰጥባቸው የሚገቡ ምልክቶች ምንድን ናቸው?
🟣የአእምሮ ጭንቀትን ለመቀነስ የጤናን እቅድ ማሻሻል
-የአእምሮ ጭንቀት ሲያጋጥመኝ ላደርገው የምችለው ልዩ ነገር አለ ?ይህንንስ የማደርግበት ቅደም ተከተል አለው?
🟣የአስጊ ሁኔታ ዕቅድ - የአእምሮ ጭንቀት አስጊ ሁኔታ ሲያጋጥመኝ ላደርገው የምችለው የተለየ ነገር አለ?
ይህ ጽሁፍ ከሊስያ ጋር በመተባበር የቀረበ ነው።
በቀጣይ ሳምንት እስካሁን ስንቀያይበት በቆየንበት ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ አዕምሮ በሚለው ዙሪያ ባለሙያ ጋብዘን፤ ከእናንተ የሚደርሱንንም ጥያቄዎች አካተን ሰፊ ማብራሪያን ይዘን እንቀርባለን፡፡
ይከታተሉን!