#NAMA

#NAMA


ለመላው የንቅናቄአችን አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ!

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ብሔራዊ ምክር ቤት ጥር 16 እና 17 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው 5ኛ መደበኛ ጉባኤው በእስር ላይ የሚገኙ የንቅናቄያችን አመራሮቻችንና አባላቶቻችንን አስመልክቶ የተለያዬ የሠላማዊ ትግል አመራጮችን ለመተግበር የድርጊት መርሃ ግብር ማስቀመጡ ይታወሳል። 

በዚህ የድርጊት መርሃግብር መሰረትም መንግስት በአንድ ወር የጊዜ ገደብ ውስጥ በግፍ ያሠራቸውን አመራሮቻችንና አባላቶቻችንን ክሳቸውን አቋርጦ የማይለቃቸው ከሆነ የካቲት 22 ቀን 2012 ዓ.ም በተመረጡ የአገሪቱ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ የመጀመሪያውን የትግል ምዕራፍ እንደሚጀምር ወስኖ ለተግባራዊነቱም ግብረ-ኃይል አቋቁሞ በመስራት ላይ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ መንግስት ለጥያቄዎቻችን በጎ ምላሽ በመስጠት የካቲት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ላለፉት 8 ወራቶች በግፍ ታስረው የነበሩ አመራሮቻችንንና አባላቶቻችንን ክሳቸውን አቋርጦ ከእስር እንዲፈቱ አድርጓል፡፡

በመሆኑም ንቅናቄአችን ይህን በማስመልከት ለየካቲት 22 ቀን 2012 ዓ.ም ጠርቶት የነበረውን ሠላማዊ ሠልፍ ከመንግሥት በኩል የታየውን በጎ ጅምርና ሌሎች ተደራራቢ የፖለቲካ ተግባራትን ከግምት በማስገባት ሰልፉ እንደማይካሄድ ወሥኗል።

በመጨረሻም ንቅናቄአችን በእስር ላይ የነበሩ አመራሮቻችንና አባላቶቻችን ዙሪያ ሲያደርግ የነበረውን ትግል በተለያዩ መንገዶች በመደገፍ በመንግስት ላይ የበኩላችሁን ጫና ስታደርጉ ለነበራችሁ አካላት በሙሉ ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል።

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!

Report Page