MoHEthiopia

MoHEthiopia


የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ

1. የብቃት ምዘና ፈተናው ከመጋቢት 20-24/2013 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን የፈተና ፕሮግራሙም እንደሚከተለው ይሆናል፡-

• ነርሲንግ ------------------------------------------ 20/07/2013 ዓ.ም

• ጤና መኮንን -------------------------------------- 21/07/2013 ዓ.ም

• ህክምና እና ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ ------- 22/07/2013 ዓ.ም

• ፋርማሲ እና አንስቴዥያ ---------------------------23/07/2013 ዓ.ም

• ሚድዋይፈሪ --------------------------------------- 24/07/2013 ዓ.ም

2. የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ ተመዛኞች በቀጥታ በተማሩበት ተቋም ወይም የተማሩበት ተቋም በሚገኝበት ከተማ በሚገኝ የመፈተኛ ጣቢያ የሚመደቡ ይሆናል ፡፡

3. ለዳግም ምዘና /Re-Exam/ በ Online Registration የተመዘገቡና ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ የመፈተኛ ከተሞችን የመረጡ ተመዛኞች በቀጥታ በመረጡት ከተማ በሚገኝ የምዘና ጣቢያ የሚመደቡ ይሆናል (የመፈተኛ ከተሞችንና ጣቢያዎችን ከዚህ በታች መመልከት ይቻላል)፡፡

· አዳማ ከተማ…………………………ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ አዳማ ካምፓስ

· አምቦ ከተማ………………………………………አምቦ ዩኒቨርሲቲ

· አርባምንጭ ከተማ……………………………አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ

· አሰላ ከተማ……………………………………….አርሲ ዩኒቨርሲቲ

· አሶሳ ከተማ……………………………………….አሶሳ ዩኒቨርሲቲ

· ባህር ዳር ከተማ………………………………..ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ

· ቡሌሆራ ከተማ…………………………………ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ

· ደብረብርሃን ከተማ…………………………ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ

· ደብረማረቆስ ከተማ………………………ደብረማረቆስ ዩኒቨርሲቲ

· ደብረታቦር ከተማ……………………………ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ

· ዲላ ከተማ……………………………………….ዲላ ዩኒቨርሲቲ

· ድሬደዋ ከተማ…………………………………ድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ

· ሀረር ከተማ………………………………………ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ

· ሀዋሳ ከተማ………………………………………ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

· ጅግጅጋ ከተማ…………………………………ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ

· ጅማ ከተማ………………………………………ጅማ ዩኒቨርሲቲ

· ጎባ ከተማ………………………………………..መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ

· መቐለ ከተማ……………………………………መቐለ ዩኒቨርሲቲ

· መቱ ከተማ………………………………………መቱ ዩኒቨርሲቲ

· ባሌ ከተማ……………………………………….ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ

· ሰመራ ከተማ……………………………………ሰመራ ዩኒቨርሲቲ

· ፊቼ ከተማ……………………………………….ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ

· ጎንደር ከተማ……………………………………የጎንደር ዩኒቨርሲቲ

· ሆሳህና ከተማ…………………………………ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

· ሶዶ ከተማ………………………………………ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ

· ዳውሮ ከተማ……………………ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዳውሮ ካምፓስ

· ወልዲያ ከተማ………………………………ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ

· ወለቂጤ ከተማ…………………………….ወለቂጤ ዩኒቨርሲቲ

· ነቀምት ከተማ…………………………….…ወለጋ ዩኒቨርሲቲ

· ቢሾፍቱ ከተማ…………………..ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ካምፓስ

· ደሴ ከተማ…………………………………….ወሎ ዩኒቨርሲቲ

· ዳንግላ ከተማ………………………ዳንግላ አንድነት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

· አዲስ አበባ ከተማ………………ስድስት /6/ የፈተና ጣቢያዎች ሲሆን /http://www.moh.gov.et/all%20AA%20Exam%20Center.pdf/ ተጭነው የተመደቡባቸውን የፈተና ጣቢያዎች ይመልከቱ፡፡


4. ለዳግም ምዘና /Re-Exam/ በ Online Registration የተመዘገቡና የመፈተኛ ከተማ አዲስ አበባ የመረጡ ተመዛኞች በአዲስ አበባ ከተማ ከተዘጋጁ ስድስት /6/ የፈተና ጣቢያዎች በአንዱ የተመደቡ ሲሆን ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝር /http://www.moh.gov.et/all%20AA%20Exam%20Center.pdf/ ላይ ተመዛኞች የተመደቡባቸውን የፈተና ጣቢያዎች መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡ (አዲስ አበባ ለመፈተን ላመለከቱ ብቻ)፡፡

5. ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ ተመዛኞች የፈተና መለያ ቁጥራቸው (Registration No) ወደየተማሩበት የትምህርት ተቋም ስለተላከ የፈተና መለያ ቁጥራቸውን ከተማሩበት ተቋም መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተመዛኞች ስልጠና የወሰዱበት ተቋም ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ (HERQA) እውቅና ያልተሰጠው ከሆነ እና እያንዳንዱ ተመዛኝ ተገቢውን መስፈርት አሟልቶ ትምህርትና ስልጠናውን ማጠናቀቁና የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ዝግጁ (Eligible) መሆኑ በኤጀንሲው ካልተረጋገጠ ፈተናውን መውሰድ የማይችል ሲሆን እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ አንድ ተመዛኝ ፈተናውን ወስዶ ቢገኝ የፈተናው ውጤት የማይያዝለት መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።

7. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115324185 መደወል ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ:- 

· ከተመደቡበት የፈተና ጣቢያ ውጭ የሚመጡ ማንኛውም ተመዛኝ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ምንጭ፦ ጤና ሚኒቴር

Report Page