Minstry of Foreign Affairs of Ethiopia

Minstry of Foreign Affairs of Ethiopia


#AmbassdorRedwanHussien

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን  መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ኤስያ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ከአምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጡ። 

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የፖለቲካ ፍላጎትን መሠረት አድርጎ በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ኢትዮጵያ እንደማትቀበል ተናግረዋል። 

አምባሳደር ሬድዋን የፖለቲካ ፍላጎት ባላቸው አካላት ገፋፊነት እና አስተባባሪነት የተላለፈው ውሳኔ በኢትዮጵያ ምድር ተፈፃሚ እንደማይሆን አብራርተዋል። 

ኢትዮጵያን አግባብነት ካላቸው ተቋማት ጋር ትብብር ስታደርግ መቆየቷን አንስተዋል። የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመመርመር ተግባራዊ ማስተካከያዎችን ለመውሰድ የሚያስችል ተቋማዊ አቅም እንዳላትም ጠቅሰዋል። ቀደም ሲል የተመድ የሰብዓዊ መብት ተቋም እና የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባደረጉት የጋራ ምርመራ የተሰጡትን ምክረ ሀሳቦችን ለመተግበር ኢትየጵያ ተግባራዊ አንቅስቃሴ በማድረግ ላይ በምትገኝበት ጊዜ የተላለፈ ውሳኔ መሆኑንም ገልጸዋል። 

ም/ቤቱ የሽብር ቡድኑ በወረራ በቆየባቸው የአማራ እና አፋር አካባቢዎች የፈጸማቸውን መጠነ ሰፊ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጥፋት በማውገዝ ምርመራ እንዲካሄድ ውሳኔ ቢያሰተላልፍ ኖሮ ተገቢና የሚያስመሰግነው እንደነበርም ገልጸዋል።  

የህወሃት ቡድን የእርዳታ አቅርቦት ለማስተጓጎል የሚወስደው የእብሪት ተግባርን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በቸልታ መመልከቱን ጠቅሰው፤ በመንግስት በኩል ግን የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚቻለውን ሁሉ ማድረጉን አመልክተዋል።

መንግስት ለሰላም ሲባል የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ያስተላለፈ ቢሆንም የሽብር ቡድኑ ግን ተመሳሳይ እርምጃ ለመወሰድ ፈቃደኛ ያልነበረ መሆኑን አስታውሰው፣ የአለም አቀፉ ማህበረሰብም የመንግስትን ውሳኔ በአዎንታዊነት በመመልከት በአንጻሩ ደግሞ በህወሃት የእብሪተዠት ተግባር እንዲገታ ጫና ባለማሳደሩ ችግሩን እንዳወሳሰበው ገልጸዋል።

የህወሃት በመንግስት የተወሰደውን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ እንደመልካም አጋጣሚ በመውሰድ በአማራና አፋር የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ወረራ በመፈፀም በንጹሃን ላይ ጭፍጨፋ መፈጸሙን፣ የመሰረተ ልማትና ሃይማኖታዊ ተቋማትን ማዉደሙን፣ ህፃናትንና ሴቶችን መድፈሩ ገልጸዋል።ይህም የህዝብ ቁጣን ቀስቅሶ በሰብዓዊ እርዳታ መስመሩን ለመዝጋት ያነሳሳበት ጊዜው እነደነበርም አስረድተዋል።  

አምባሳደር ሬድዋን በማብራሪያቸው የህወሓት አሸባሪ ሀይል በደረሰበት ምት ይዟቸው የነበሩ አብዛኛው የአፋር እና የአማራ አካባቢዎችን በማስለቀቅ በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ገልፀዋል። ይህም ቡድኑ ለሰላም ሲል በወረራ ከያዝኳቸው አካባቢዎች ለቅቂያለሁ ማለቱ ከተጨባጩ እውነታ ጋር የሚቃረን ስለመሆኑም አንስተዋል።

አምባሳደር ሬድዋን መንግስት ቡድኑ በሚሸሽባቸው እያንዳንዱ የትግራይ መንደሮች እግር በእግር በመከተታል የመግባት ፍላጎት የሌለው መሆኑን ጠቁመው፣ ነገር ግን ቡድኑ መቸውም ቢሆን መልሶ ጥቃት የማድረስ አቅሙ የተዳከመ መሆኑ ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። 

አክለውም የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትን ማስጠበቅ የመንግስት ኃላፊነት እንደመሆኑ መጠን፣ ትግራይን ጨምሮ በማንኛውም ሀገሪቱ አካባቢዎች ሰራዊቱን የማስፈር መብት እንዳለው አመላክተዋል።

በቀጣይ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ያለመ ሁሉን አካታች ዉይይት እንዲኖር ማንኛዉም በአገሪቱ ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል አካል የሚሳተፍበ የህገ መንግስት ማሻሻያን ጨምሮ በሀገሪቱ ስምምነት ያልተደረሰባቸው ጉዳዮችን የተመለከቱ ጉዳዮች ለውይይት ክፍት እንደሚደረጉ ገልጸዋል።

በመጨረሻም ከአምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ክቡር አምባሳደር ሬድዋን ምላሽ ተሰጥቷል።

(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)

@tikvahethiopia

Report Page