Media DMU39

Media DMU39


የጨረታ ማስታወቂያ
ብግጨ 39/2012
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2012 የበጀት ዓመት ከመንግስት በተመደበለት በጀት ያለቀለት ድራማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ሥራውን ለመሥራት የሚፈልጉ ተጫራቶች፡-

በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማቅረብ የሚችሉ፣
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00/ አስር ሺህ ብር / በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሠርተው ማቅረብ ሲኖርባቸው በጥቃቅን የተደራጁ ከአደራጃቸው የመንግስት መ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም በማሠራት ማቅረብ አለባቸው፣
አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀለት ከ7/ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት፣
ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 እና አዲስ አበባ አራት ኪሎ ከቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ሮሚና ካፌ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በመቅረብ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ/ ብር በ መክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፣
ተወዳዳሪ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመመላትና በማሸግ በ6ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡59 ሰዓት ድረስ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ደረስ በመቅረብ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
ጨረታው በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡30 ሰዓት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቶች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቶች ፖስታን ጨምሮ ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
የጨረታውን ፋይናንሽያል ኦርጅናል ዶክመንቶች እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የመ/ቤቱን ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ አንድፖስታሽማሸግማቅረብ ሲኖርባቸው ፋይናንሽያል ዶክመንቶች ከኦርጅናሉ በተጨማሪ አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ መሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ማሣሰቢያ፡- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
ለበለበጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 05877166-91 ደብረ ማርቆስ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 15 ቀን 2012

Deadline: June 7, 2020


© walia tender

Report Page