Med ammanuel specialized hosp12

Med ammanuel specialized hosp12


የጨረታ ማስታወቂያ

የአማኑኤል አእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ 2012 በጀት ዓመት የመድሃኒት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ:

በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ
የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ያላቸው
Vat ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ በተቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ሊስት ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ ወይም በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር www.ppa.gov.et ላይ መመዝገብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዱን የሚመለስ ብር 10,000 / አስር ሺህ ብር በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፤
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 / ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዳችሁን ለየብቻ 2 ቅጂዎች ቴክኒክ ዋናና ኮፒ እና ፋይናንሽያል ሰነዳችሁን ዋናና ኮፒ በማለት እያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅታችሁን ማህተምና ፊርማ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአማኑኤል አዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በግዢ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 71 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ትችላላችሁ፡፡
ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ሆኖ በ15 ኛው ቀን ላይ ከቀኑ 10:30 ሰዓት የጨረታ ሣጥን ተዘግቶ በ16 ኛው ቀን በ3 ፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ዳ/ዳ ቢሮ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት የሚከፈትና የሚዘጋ ይሆናል፡፡

ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግዥ ዳ/ዳይሬከተር ቍጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቀጥር፡- 0118685387/0112788056 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- አሸናፊው ድርጅት ዕቃውን አማ/አዕ/ስፔ/ሆ/ል መ/ቤት ድረስ የሚያደርስ መሆኑን እናሳውቃስን፡፡

የአማኑኤል አእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 26 ቀን 2012

Deadline: June 17, 2020


© walia tender

Report Page