Make Way
VSO, RTGወጣቶችን ማብቃት፡ ለሥነ ፆታ እና ሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች መሻሻል ቁልፍ ነው
ወጣቶች ከዓለም ህዝብ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ይይዛሉ፣ ነገር ግን ብዙውን ጊዜ እንደ ተዋልዶ ጤና ያሉ ወጣት ተኮር ጉዳዮች ላይ ያላቸው ተሣትፎና ተሰሚነት በእጅጉ የተገደበ ነው።
ትርጉም ያለው የወጣቶች ተሳትፎ ማለት ወጣቶችን ወደ ውይይት መድረክ ከመጋበዝ ወይም አስተያየታቸውን ከመጠየቅ ያለፈ የተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች አደረጃጀት፣ አቅርቦት እና የአገልግሎት ግምገማ ላይ በንቃት እንዲሁም በባለቤትነት እንዲ ሳተፉ ማድረግ ማለት ነው።
ለምን አስፈላጊ ሆነ?
ወጣቶች የተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን በማግኘት ረገድ ልዩ ፈተናዎች ያጋጥሟቸዋል ከነዚህም ውስጥ፡-
- ከአገልግሎት ከአቅራቢዎች የተሳሳተ አመለካከቶች
- ሚስጥራዊነት ማጣት
- ስለመብቶቻቸው የግንዛቤ እጥረት
- በአሉታዊ ባህሎች መገለል የሚጠቀሱ ናቸው።
ወጣቶች ትርጉም ባለው መልኩ ሲሳተፉ የተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ይበልጥ ተስማሚ፣ ተደራሽ እና ውጤታማ ይሆናሉ። የወጣቶች ተደራሽነት፣ ትምህርት እና የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያሻሽሉ አዳዲስ አመለካከቶች፣ ትጨባጭ የህይወት ተሞክሮዎችን ያመጣሉ።
ትርጉም ያለው ተሳትፎ ምን ይመስላል?
- የወጣቶች አማካሪ ቦርዶች፡ በጤና ፕሮግራም እቅድ ውስጥ ለወጣቶች የመወሰን ስልጣን መስጠት።
- የአቻ ትምህርት ፕሮግራሞች፡- ወጣቶች እንዲማሩ እና እንዲደጋገፉ ማድረግ።
- ዲጂታል ተሳትፎ፡- ማህበራዊ ሚዲያን፣ መተግበሪያዎችን እና የበይነ መረብ መድረኮችን በመጠቀም ወጣቶችን ማግኘት እና መስማት።
- የግብረ-መልስ ሥርዓቶች፡- አገልግሎቶችን ለማሻሻል የወጣቶች ግብአቶችን በመደበኛነት መሰብሰብ እና መተግበር።
- አካታች አገልግሎቶች፡- ክሊኒኮች ሚስጥራዊነታችው የተጠበቀ፣ የማይፈርጁ እና ለሁሉም ወጣቶች እና ለተደራሸ ላልሆኑ ቡድኖች አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸውን ማረጋገጥ።
ውጤቶቹ?
ወጣቶች በንቃት እና በባለቤትነት ሲሳተፉ፡
- ብዙ ወጣቶች የተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን ይጠቀማሉ
- በጤና አጠባበቅ ሥርዓቶች ላይ እምነት ይጨምራል
- ጎጂና አደገኛ ባህሪያትን ይቀንሳል
- ወጣቶች በማህበረሰባቸው ውስጥ ንቁ የጤና ቀስቃሽ ወይም ትሟጋች ይሆናሉ
ወጣቶች ተጠቃሚ ብቻ አይደሉም ለውጥ ፈጣሪዎች ናቸው። ውጤታማ፣ አካታች እና ወጣቶችን ያማከለ የተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን ለመገንባት በየደረጃው ወጣቶችን ማሳተፍ አለብን።
እናዳምጥ! እናካት ! አቅም እንፍጠር!።