Make Way
VSO, RTGድርብርብ ቀንበር ያለባቸው ወጣቶችን አካታች ያደረገ የማህበረሰብ ሀሳብ መስጫ ካርድ ለተዋልዶ ጤና አገልግሎት በኢትዮጵያ
‘የተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን አካታች፤ ለወጣቶች ምቹ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት ማድረግ’
በተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ላይ ድርብርብ ቀንበር ያለባቸው ወጣቶችን አካታች ያደረገ የማህበረሰብ ሀሳብ መስጫ ካርድ ምንድን ነው?
ድርብርብ ቀንበር ያለባቸው ወጣቶችን አካታች ያደረገ የማህበረሰብ ሀሳብ መስጫ ካርድ ወጣቶችን፣ የተገለሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን፣ አገልግሎት ሰጭዎችን እና ማህበረሰቡን ባሳተፈ በእውነተኛ ተሞክሮዎች እና በአካታች ውይይት ላይ በመመስረት የፆታዊ እና የተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን ለመገምገም እና ለማሻሻል የሚያስችል አሳታፊ የማህበራዊ ተጠያቂነት ማስፈኛ ዘዴ ነው።
የማህበረሰብ ሀሳብ መስጫ ካርድ በተዋልዶ ጤና አገልግሎት ላይ ያለው አስፈላጊነት?
የተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ብዙውን ጊዜ የሚከተሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች በአገልግሎታችው ተደራሽ የማድረግ ውስንነት ይታይባቸህዋል፡-
- በጉርምስና እድሜ ላይ የሚገኙ ልጃገረዶችን
- አካል ጉዳተኛ ወጣቶችን
- በቁጥር አነስተኛ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን
- በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን
- የተፈናቀሉና በመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን
- በገጠር እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎችን
ስለሆነም ለእነዚህ ተደራራቢ የችግር ቀንበሮች ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ፍትሃዊ፣ አካታች እና ተደራሽነት ያለው የጤና አገልግሎት ማስፈን አስፈላጊ ነው።
የማህበረሰብ ሀሳብ መስጫ ካርድ ትግበራ በ ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ላይ እንዴት ይሰራል?
የመብቶች ግንዛቤ
- የተገለሉ ወጣቶችን በ ተዋልዶ ጤና መብታቸው ላይ ማስተማር እና ማብቃት ብሎም የተሻለ አገልግሎት እንዲጠይቁ ማድረግ።
የአገልግሎት ግምገማ
- ተጋላጭ ወጣቶች የማህበረሰብ ሀሳብ መስጫ ካርድ ያዘጋጃሉ፤ የውጤት መመዘኛ አመልካቾችን ያሥቀምጣሉ።
- የጤና ባለሙያዎች የአገልግሎት ጥራትን በራሳቸው ይገመግማሉ።
የገጽ ለገጽ ውይይት
- የውይይት መድረኮቹ በወጣቶች እና በአገልግሎት ሰጪዎች መካከል ያለውን የአመለካከት ክፍተት በማስተካከል ችግሮችን መፍታት ላይ ያተኩራል።
የጋራ የድርጊት መርሃ ግብር እና የማህበራዊ ተጠያቂነት ኮሚቴ ምሥረታ
- ለወጣቶች፣ ለአገልግሎት ሰጪዎች፣ ለአካባቢ መሪዎች እና ለማህበረሰብ ተወካዮች በተሰጡ ሚናዎች በጊዜ የተገደበ የድርጊት መርሃ ግብር ማስቀመጥ። የማህበራዊ ተጠያቂነት ኮሚቴ መመስረት፡፡
- የማህበራዊ ተጠያቂነት ኮሚቴ የተቋቋመው የጋራ የድርጊት መርሃ ግብር አፈጻጸሙን ለመቆጣጠር እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ነው።
- መደበኛ ግምገማዎች እና በአገልግሎት ላይ የሚታዩ ለውጦችን መከታተል።
- የማህበራዊ ተጠያቂነት ኮሚቴ ወጥነት ባለው መልኩ ለውጦችን መገምገም እና ዕቅዶችን መከለስና ማስተካከል፣ ይህም የረጅም ጊዜ አገልግሎት መሻሻልን ያረጋግጣል።
ድርብርብ ቀንበር ያለባቸው ወጣቶችን አካታች ያደረገ የማህበረሰብ ሀሳብ መስጫ ካርድ በኢትዮጵያ
- የማህበረሰብ ሀሳብ መስጫ ካርድ የተተገበረው በሪዲም ዘ ጀነሬሽን በሜክ ዌይ ፕሮግራም ከቪኤስኦ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ሲሆን ትኩረቱም የማህበራዊ ተጠያቂነት ማስፈኛ ዘዴ በመጠቀም የልጃገረዶችን፣ የአካል ጉዳተኛ ወጣቶችን እና በቂ አገልግሎት ያላገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን ድምጾች እንዲሰሙ በማድረግ የሥነ ፆታ እና የተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ፍታዊና ተደራሽ ማድረግ ነው፡፡
ድርብርብ ቀንበር ያለባቸው ወጣቶችን አካታች ያደረገ የማህበረሰብ ሀሳብ መስጫ ካርድ የታዩ ውጤቶች እና ተፅዕኖ
- በግንዛቤ ማስጨበጫ እና ቅስቅሳ የመጡ ውጤቶች
- መንግስት የጤና ባለሙያዎች ቅጥር እና ስልጠና እንዲከናወን ቅስቅሳዎች ተከናውነዋል።
- የማህበረሰብ ሀሳብ መስጫ ካርድ የቅስቀሳ ጥረት በኢትዮጵያ በወጣቶች ጤና ፋይናንስ ዙሪያ ቀጣይነት ያላቸው ክፍተቶች ላይ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷል።
- የተመዘገቡ የአገልግሎት ማሻሻያዎች
- ለወጣቶች ምቹ የሆኑ የተዋልዶ ጤና አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎችን ማደስና ወደ ሥራ ማስገባት፡፡
- የ24/7 አገልግሎት አቅርቦት ማስተዋወቅ
- ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሲሲቲቪ ካሜራዎች በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መግጠም፡፡
- ለወሊድ ጊዜ የሚሆኑ አልጋዎች እና የአልትራሳውንድ ማሽኖች እንዲገዙ ማድረግ፡፡
- የመጸዳጃ ቤቶች ግንባታ።
- ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ የሕንጻ መወጣጫ ማዘጋጀት።
- የጤና ሰራተኛ አቅም ማሻሻል
- ለአገልግሎት ሰጪዎች የአካታችነት እንክብካቤ ስልጠና መስጠት
- አካታች የተግባቦት ክህሎትን የሚያሳድጉ ዘዴዎችን ተደራሽ ማድረግ
- መደበኛ የወጣቶች የተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ሥልጠና መስጠት
- የአገልግሎት ጥራት እና ዝግጁነት
- አስፈላጊ ለሆኑ የተዋልዶ ጤና መድሃኒቶች የድንገተኛ አደጋ ክምችት ስርዓት ተዘርግቷል።
- ዘላቂነት እና መስፋፋት።
- በሌሎች የጤና ማዕከላት የማህበረሰብ ሀሳብ መስጫ ካርድ ትግበራን መስፋፋት፡፡
- የማህበረሰብ ድምጾች
"ሁላችንም አንድ አይነት መሰናክሎች አያጋጥሙንም፤ ስለዚህ ይህ አስራረ ተደራራቢ የችግር ቀንበሮች ትኩረት ያደረገ መፍትሔ አገልግሎቶችን ብቻ ሳይሆን ስርዓቶችን እንድንለውጥ ይረዳናል።"
"አሁን ያለ ፍርሃት ወይም ሀፍረት ወደ ክሊኒኩ መሄድ እችላለሁ። የጤና ባለሞያዎቹም እንዴት እንደሚያናግሩን ያውቃሉ እናም ደህንነት ይሰማናል."
የወጣቶች ተሳታፊዎች