#MT

#MT

Mosaic Technologies

ድርጅቴ ድረ-ገጽ (Website) ቢኖረው ምን ይጠቅመኛል?

በሀገራችን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል፡፡ በዘንድሮ በጀት አመት ኢትዮ ቴሌ 23.8 ሚሊዮን የኢንተርኔት ተጠቃሚ እንዳለ አስታውቋል፡፡ 

የብሮድ ባንድ ተጠቃሚም 212.2 ሺ ላይ ደርሷል፡፡ በሚቀጥሉት አመታትም መንግሥት ባቀዳቸው የፕራይቬታይዜሽን ሥራዎች ሁለት የቴሌኮም ድርጅቶች እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡ 

ይህም የኢንተርኔት ተጠቃሚውን ቁጥር በእጅጉ እንደሚጨምረው እሙን ነው፡፡ የዲጂታል ገቢያውን የሚያጠናክሩ ህጎቸ መርቀቃቸው ደግሞ ለዘርፉ እድገት ወሳኝ ሚናን ይጫወታል፡፡ 

ታዲያ በዚህ ጊዜ እርሶ ለድርጅቶ፣ ለንግድ ሀሳቦ ምን አስበዋል? ዘመኑ ከሚጠይቀው የዲጂታል ግንኙነት ጋርስ እንዴት ሊጓዙ አቅደዋል? በተከታዮቹ አምስት ነጥቦች ለምን ዌብሳይት ማሰራት እንዳለቦ እንግለጽሎት

1. በዲጂታል አማራጮች መገኘት (Digital Presence )

ለንግድ ቤቶ ሱቅ እንደሚከራዩና(እንደሚገነቡ)፣ ለፋብሪካዎ ማምረቻ እንደሚያንጹ፣ ምርቶን ለማስተዋወቅና ለመሸጥ ገቢያ እንደሚወጡ እንዲሁ በራሶት ድረ-ገጽ (Website) በቦታ ሳይገደቡና ብዙ ወጪ ሳይወጡ ሥራዎትን ያለ ገደብ ማስተዋወቅ ይችላሉ፡፡

2. ስለ ምርቶ፣ ድርጅቶና ስለ ሥራዎ ትልቅ አስረጂ ይሆኖታል

እርሶ ሁሉም ቦታ ተገኝተው ስለ ሥራዎ ማስረዳት ላይችሉ ይችላሉ፣ ሰው ቀጥረውም ምርቶን ለማስተዋወቅና ለመሸጥ አቅም ሊገድቦ ይችላል፡፡ ድረ-ገጽ (Website) ቢኖሮት ግን ደንበኛዎ ያለ ችግር ያለ ገደብ ስለ አገልግሎቶ በቂ መረጃ ማግኘት ይችላል፡፡ ይህም ደንበኛዎትን ያረካል የእርሶንም ድካም ይቀንሳል፡፡ ውጤቱም በጣም ያማረ ይሆናል፡፡

3. ስለ ደንበኛዎ መረጃ ማግኘት ይችላሉ

ድረ-ገጾ በጥሩ ሁኔታ ካበለጸጉ ደንበኛዎ ያለውን አስተያየት፣ ከየት አከባቢ ደንበኛዎ እንደሚበዛ፣ ብዙ ተጠቃሚ ያለው ምርቶ የቱ እንደሆነ፣ ምንያህል አገልግሎቶ ተደራሽ እንደሆነ በማወቅ በቀላሉ ድርጅቶ ያለውን ትርፋማነት መጨመር ይችላሉ፡፡

4. የድርጅቶን ገጽታ በጥሩ ይገነባል ( Branding )

ጥሩ ዌብሳይት የጠንካራ ድርጅት አንዱ መገለጫ ነው፡፡ በዌብሳይቶ በአገልግሎቶ የተደሰቱ ምስክሮች አስተያየት ከተካተተ ለሌሎች ደንበኞች በድርጅቶ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ያስችላል፡፡ ከእርሶ ጋር በስራ ተገናኝተው አብረው እየሰሩ ያሉ ድርጅቶችን በመግለጽ ምን ያህል ድርጅቶ ብቃት ያለው እንደሆነ ሊያሳዩ ይችሉበታል፡፡

5. ምርትና አገልግሎቶ በሰው ዘንድ ያለውን ተቀባይነት ይጨምራል

የሚሰጡትን አገልግሎት በአግባቡ የሚገልጽ ድረ-ገጽ ካሎት ደንበኛዎ ባለበት ሆኖ ስለምርቶ በቂ እውቀት መያዝ ይችላል፡፡ ይህ ማለት የእርሶን ሥራ ከማቅለሉም በላይ ደንበኛዎ በምርቶ ላይ ያለው እምነት እንዲጠነክርና ግንኙነቱም ጠንካራ እንዲሆን ያስችለዋል፡፡

ለውጤታማነቶ  አብረን እንሥራ!

Report Page