Lease debre birhan1

Lease debre birhan1

Walia Tender

የመሬት ሊዝ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ዙር...13ኛ
የጨረታው አይነት ..መደበኛ
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 እና ይህንኑ አዋጅ ለማስፈፀም የአብክመ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ ባወጣው ደንብ ቁጥር 103/2004 በክፍል 3 በአንቀፅ 10 በንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ”ሀ” እስከ “ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለልዩልዩ አገልግሎቶች ማለትም/ ለመኖሪያ፣ ለንግድ፣ ለማህበራዊ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል:: በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ሰው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 250/ ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 23 ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን:
ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች ሁለት የተለያዩ ተመሳሳይ ፖስታዎችን በማዘጋጀት 1ኛ ክፍል ሁለት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን እና ክፍል ሶስት የጨረታ ሀሳብ ማቅረቢያ ሰነዱን 2ኛ ሲፒኦ ሁለቱን ሰነዶች አንዳንድ ኮፒ በማድረግ ኦርጅናሉን ለብቻ ኮፒውን ለብቻ በተለያዩፖስታዎች በማሸግና በፖስታዎቹ ላይ ኦርጅናል ወይም ኮፒ በማለት ለይቶ በመፃፍ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፖስታውን እስከ 10ኛው (አስረኛው) ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 1 ኦርጅናሉን ሰነድ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ኮፒውን ሰነድ ደግሞ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
ጨረታው የሚዘጋው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ 11 ፡00 ሰዓት ላይ ይሆናል::
ቦታውን መጐብኘት ለሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለፀው መርሃ ግብር መሰረት የምናስጐበኝ ይሆናል፡፡
. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው አዳራሽ፡፡ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11 ኛው የስራ ቀን ከጠዋት 4 ፡00 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
.የጨረታ መከፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ እና በጽ/ቤቱ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ እንዲሁም በቢሮው E-mail: nslando6gmail.com ማግኘት ይችላሉ::
ለጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ የተያዘ የcpo ገንዘብ በጨረታው ለተሸነፉ እስከ 6 ወር ካልወሰዱ ወደ መንግስት ካዝና ገቢ ይሆናል፡፡
መስሪያቤቱጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡0116811074/ 0116813072 ደውሎ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ ቤት



Posted: አዲስ ዘመንግንቦት 26 ቀን 2012

Deadline: June 12, 2020


© walia tender


Report Page