Lease bure 3

Lease bure 3


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የቡሬ ከተማ አስ/ቤ/ኮ/አገ/ጽ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 721/04 አንቀጽ 1 መሰረት የ2012 ዓ/ም 1ኛ ዙር አገራዊ ፋይዳ ላላቸው ለመደበኛ ጨረታ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዓመታዊ የቦታ ሊዝ ዋጋ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ሁሉ መጫረት የሚችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ተጫራቾች በሚዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ሰነዱን ሞልተው ጨረታው በወጣ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
በመጀመሪያ ዙር ለአንድ ቦታ ከ3 ተጫራቾች በታች ከቀረበ ጨረታው አይከናወንም፡፡
የጨረታ አሸናፊ የሚሆነው ከቀረቡት ተጫራቾች ውስጥ ለቦታው በካሬ ሜትር ከፍተኛውን ዓመታዊ የቦታ የሊዝ ክፍያ ለመክፈል ያቀረበ/ች/ ይሆናል፡፡
በአንድ ቦታ ላይ ሁለት እና ከዚያ በላይ ተጫራቾች ተመሣሣይ ዓመታዊ የቦታ ሊዝ ክፍያ ለመክፈል ካቀረቡ አሸናፊው በእጣ ይለያል፡፡ ሆኖም ተመሣሣይ ዓመታዊ ሊዝ ለመክፈል ያቀረቡት ተጫራቾች ወንድና ብቸኛ ሴት ከሆኑ ቅድሚያ ለሴት ይሰጣል፡፡
የጨረታ ውጤት የሚፀድቀው በማኔጅመንት ኮሚቴ ሲሆን የጨረታ አስፈፃሚ ኮሚቴው በአራት የሥራ ቀናት ውስጥ ያጠናቅቃል፡፡
አሸናፊው ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል በቡሬ ከተማ አገልግሎት በአካል ቀርቦ እስከ 10 ቀን ውል መዋዋል አለበት፡፡
የጨረታ አሸናፊው የይዞታ ምስክር ወረቀት በሊዝ ስሪት መሰረት ተዘጋጅቶ ይሰጣል፡፡
የግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ ጊዜ በአዋጅ ቁጥር 721/04 እና በደንብ ቁጥር 103/04 የተደነገጉት እንደተጠበቁ ሆኖ መመሪያ ቁጥር 1/2005 አንቀጽ 47/49 ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
ለጨረታ የቀረበው የቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት ከ5 በመቶ ያላነሰ በባንክ የተመሰከረለት/ ሲፒኦ/ አስርቶ ከሃሣብ እና ከዋና ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ኦርጅናል ዋጋ የተሞላበትን አያይዞ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ጽ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የቡሬ ከተማ አስ/ ቤ/ ኮ/ አገ/ ጽ/ ቤት




Posted: በኩር ግንቦት 10 ቀን 2012
Deadline: June 2, 2020


© walia tender

Report Page