Lease ataye1

Lease ataye1


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

/ ጨረታ ቁጥር 04/2012

በአብክመ በሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት በከተማው ውስጥ የሚገኙ የንግድ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአልሚዎች በሊዝ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች መሰረት በማድረግ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፡

በአጣዬ ከተማ 02 ቀበሌ በከብት ህክምና ጀርባ በሚካሄድ መንገድ ከአቡከር ተራራ ስር ያለው ቦታው የፕላን ምደባ መኖሪያ፣ የቦታ ስፋት 200 ካሜ፣ የቦታ ደረጃ 3ኛ፣ የሕንፃ ከፍታ G+0 እና ከዚያ በላይ የቦታ ኮድ 01፣
በአጣዬ ከተማ 02 ቀበሌ ከስታዲየምጀርባ አቶ ሰይድ የኖሩበት ቤት ያለውን የፕላን ምድባ ቅይጥ፣ የቦታ ስፋት 271.5 ካ.ሜ፣ የቦታ ደረጃ በንግድ 3ኛ፣ የሕንፃ ከፍታ G+1 እና ከዚያ በላይ፣ የቦታ ኮድ 02፣
በአጣዬ ከተማ 01 ቀበሌ ዝግባ ሰፈር ከታችኛው ተፋሰስ በኩል የማህበር ቤት አካባቢ ያለው የፕላን ምድባ መኖሪያ፣ የቦታ ስፋት 131.2 ኪሜ፣ የቦታ ደረጃ 2ኛ፣ የሕንፃ ከፍታ G+0 እና ከዚያ በላይ የቦታ ኮድ 03፣
በአጣዬ ከተማ 01 ቀበሌ ዝግባ ሰፈር ከታችኛው ተፋሰስ በኩል የማህበር ቤት አካባቢ ያለው የፕላን ምድባ መኖሪያ፣ የቦታ ስፋት 200 ካሜ፣ የቦታ ደረጃ 2ኛ፣ የሕንፃ ከፍታ G+0 እና ከዚያ በላይ የቦታ ኮድ 04፣
በአጣዬ ከተማ 01 ቀበሌ ማስረሻ ወፍጮ ከነበረው ጀርባ በቀበሌው ቤት ጀርባ ያለው የፕላን ምድባ ንግድ፣ የቦታ ስፋት 133 ካሜ፣ የቦታ ደረጃ 2ኛ፣ የሕንፃ ከፍታ G+1 እና ከዚያ በላይ የቦታ ኮድ 05፣


የጨረታ መነሻ ዋጋ በግልጽ ጨረታ ሆኖ በቦታው በሊዝ መነሻ ዋጋ ይሆናል፡፡
የጨረታ አሸናፊ የሆነው ግለሰብ ወይም ድርጅት የሚፈለግበትን ቅድመ ክፍያ መጠን ማሸነፉ እንደተገለጸለት ወዲያውኑ 20% ከዚያ በላይ ቅድሚያ ይከፍላል፡፡

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚቀርበው ገንዘብ ወይም ሌላ የዋስትና ማረጋገጫ ሰነድ ከጠቅላላው ዋጋ ላይ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠው ቼክ ወይም ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዝብ ብቻ 5% በአጣዬ ከተማ አስ/ገ/ ኢ/ት/ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ አድርጎ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00( ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል በአጣዬ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነዱ የሚመለሰው በአገልግሎት ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
ተጫራቾች ቦታዎችን ተዘዋውረው በአካል ማየትና ማጎብኘት ይችላሉ፡፡

የጨረታ መክፈቻና መዝጊያ ጊዜን በተመለከተ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡

የጨረታ ሰነድ የሚዘጋበት ቀን በ10 ኛው ቀን 11 ፡30 ሰዓት ሆኖ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ውክልና ያላቸው በተገኙበት በማግስቱ ጠዋት በ3 ፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ጨረታ የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ሲፈልጉ በስልክ ቁጥር፡- 033 661 0688/033 661-0011 ደውለው ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡



በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን የአ ጣዬ ከተማ አስተዳደር ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ ቤት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 20 ቀን 2012

Deadline: June 6, 2020


© walia tender

Report Page