Lease 03

በገጠር መሬት የግብርና ኢንቨስትመንት ልማት ለመሳተፍ መወዳደር ለሚፈልጉ ባለሀብቶች
የወጣ የመሬት አቅርቦት ማስታዎቂያ
የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ በተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች በመሬት ባንክ ውስጥ የሚገኙ የመንግስት መሬቶችን በገጠር መሬት የሊዝ ህግ በውድድር ስርአት ለባለሃብቶች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የእርሻ ኢንቨስትመንት መሬት ፈላጊዎች በሙሉ ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለጹትን መስፈርቶች ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ የተዘጋጀ የኘሮጀክት ሀሳብ ሰነድ እና አሰፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን አያይዞ በማቅረብ መመዝገብና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የእርሻ ኢንቨስትመንት መሬት የሚፈልግ ባለሃብት (ድርጅት) ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር አንድ ወር ጊዜ ውስጥ የኘሮጀክት ሀሳብ (Business plan) ከማመልከቻ ጋር ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ቢሮ ማቅረብ አለበት፡፡ የኘሮጀክት ፕሮፓዛል (ሃሳብ) በአማርኛ ወይም በእንግሊዘኛ ቋንቋ አዘጋጅቶ ማቅረብ አለበት፡፡ አመልካቹ የሚወዳደርበትን መሬት ለይቶ ማቅረብ አለበት፤ ማለትም መሬቱ የሚገኝበት ዞን፣ወረዳ፣ቀበሌ፣ልዩ-ቦታ፣ የመሬቱ ስፋት በሄ/ር እና ለምን አገልግሎት እንደሚውል /የመሬት አጠቃቀሙ/ እና በማስታወቂያው ላይ የተጠቀሰው የቦታው ተራ ቁጥር መገለጽ አለበት፡፡
አንድ ተወዳዳሪ ባለሀብት መወዳደር የሚችለው በአንድ መሬት ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ከአንድ በላይ በሆነ መሬት አመልክቶ ቢገኝ ሙሉ በሙሉ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን በፊት ባሉት 3 ተከታታይ ወራት ጊዜ ውስጥ የፋይናንስ አቅማቸውን የሚያሳይ የባንክ ስቴትመንት ተወዳዳሪ ባለሀብቶች ማቅረብ አለባቸው፡፡
አመልካቹ አካል አክሲዩን /ማህበር/ ከሆነ በሚመለከተው አካል የጸደቀ የመመስረቻ ጽሁፍና መተዳደርያ ደንብ እና ህጋዊ ሰውነት ያገኘበትን ሰነድ ማቅረብ አለበት፡፡
አመልካቾች ጠቃሚ ናቸው የሚሏቸውን ሌሎች ተጨማሪ የሰነድ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
አመልካቾች የተንቀሳቃሽ ንብረት ማለትም እንደ እርሻ መገልገያ ማሽነሪ እና የመሳሰሉትን ያላቸው ተወዳዳሪዎች የባለቤትነት ማስረጃዎች ህጋዊ ስልጣን ካለው ተቋም ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በአንድ መሬት ላይ ብቸኛ ተወዳደሪ በሚቀርብበት ጊዜ፣ የቴክኒክ ግምገማ ከ75 % ውስጥ 37.5%፣ እንዲሁም የፋይናንስ አቅም (የባንክ ተቀማጭ ገንዘብ) በተመለከተ ደግሞ ከ25% ውስጥ 12.5 % ወይም በሁለቱም የመገምገሚያ መስፈርቶች በእያንዳንዱ 50% (ሃምሳ ከመቶ) እና ከዛ በላይ ነጥብ ካመጣ የውድድሩ አሸናፊ ይሆናል፡፡
በተራ ቁጥር 7 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በአንድ መሬት ላይ ከአንድ በላይ ተወዳዳሪ በሚኖርበት ጊዜ፣ ተወዳዳሪዎች በሚያገኙት የነጥብ ብልጫ የሚለዩ ይሆናል፡፡ ሆኖም ተወዳዳሪዎች በቴክኒክ እና በፋይናንስ ግምገማ ውጤት በእያንዳንዱ ከ50 በመቶ በታች ካመጡ ፕሮጀክቱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
በአንድ መሬት ላይ ከአንድ በላይ ተወዳደሪዎች ተወዳድረው አኩል ውጤት ካገኙ ለሴት ተወዳደሪዎች ፣በንግድ ማህበራት (አክሲዮን፣ሽርክና፣ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና የመሳሰሉት) ተደራጅተው ለቀረቡ ባለሃብቶች እንደቅደም ተከተላቸው ቅድሚያ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ሆኖም በአንድ መሬት ሴት ተወዳዳሪዎች ከሴት ተዎዳዳሪዎች እና በንግድ ማህበር የተደራጁ ተወዳዳሪዎች ከንግድ ማህበር ከተደራጁ ተወዳዳሪዎች እኩል ውጤት ካገኙ በባንክ ስቴትመንት የተሻለ የገንዘብ መጠን ያሳየው (በባንክ ስቴትመንት የተሸለ ነጥብ የተሰጠው) ቅድሚያ ይሰጠዋል ፡፡
በተራ ቁጥር 9 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በግል ደረጃ ለሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች እኩል ውጤት ቢያመጡ ተወዳዳሪወች በተገኙበት በዕጣ የሚለዩ ይሆናል፡፡
የውጭ ሃገር የባንክ ስቴትመንት የሚያቀርቡ ባለሃብቶች የሚያቀርቡትን የባንክ ተቀማጭ የገንዘብ አቅም በሃገር ውስጥ ጉዳዩ በሚመለከተው ህጋዊ ተቋም የተገናዘበ ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ
የማወዳደሪያ መስፈርቶችን በተመለከተ ለኢንቨስትመንት እንዲውል ተሻሽሎ የወጣ የገጠር መሬት አሰጣጥ እና አጠቃቀም መመሪያ ቁጥር 08/2011 ዓ.ም መመልከት ይቻላል፡፡
ለውድድር የሚቀርቡ አስፈላጊ መረጃዎችን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ለውድድር የሚቀርብ የባንክ ስቴትመንት ማስታወቂያው እስከ ወጣበት ቀን ድረስ ያልተቆራረጠ ወደ ኋላ የ3 ተከታታይ ወራት መቅረብ ይኖርበታል፡፡
በውድድር ጊዜ የሚቀርብ የበጎ አድራጎት የምስክር ወረቀት ማስታወቂያው ከመውጣቱ በፊት የተሰጠ መሆን ይኖርበታል፡፡
ማስታወቂያ ከወጣ ከአንድ ወር በኋላ የሚቀርብ ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
በተራ ቁጥር 2 እና 3 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ የምዝገባው ቀን ካለፈ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም ሰነድ እና ተወዳደሪዎች ከተመዘገቡ በኋላ የምዝገባ ጊዜ ባይጠናቀቅም የተጨማሪ ሰነድ ይያዝልኝ ወይም ቀድሞ ገቢ የተደረገ ሰነድ ይቀየርልኝ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፡፡
አመልካቾች የሚያቀርቡት የኘሮጀክት ሃሳብ ካመለከቱበት ዞን፣ወረዳ፣የመሬት ስፋት፣የመሬት አጠቃቀም እና ተራ ቁጥር ጋር የማይገናዘብ ከሆነ ውድቅ ይሆናል፡፡
አመልካቾች የፕሮጀክት ሃሳባቸውን ማስታወቂያው በወጣ ባሉት ለተከታታይ 30 ቀናት ሆኖ ፕሮጀክቱን የሚያቀርቡት በመንግስት የስራ ሰዓት ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይሁን እንጅ የመጨረሻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3 ፡00 ሰዓት በፊት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ነግር ግን ከ3 ፡00 በኋላ የሚቀርብ የፕሮጀክት ሃሳብ ተቀባይነት የለውም፡፡
ከዚህ በፊት በተለያየ ጊዜ ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ቢሮ መሬት እንዲሰጣቸው ያመለከቱ እና ይሰጠናል በማለት በመጠባበቅ ያሉ ባለሃብቶች /ድርጅቶች/ ማሰታወቂያው ላይ በዝርዝር ከተገለጹት መሬቶች አንዱን በመምረጥ ከዚህ በፊት ያቀረቡትን የፕሮጀክት ሃሳብ አስተካክለው ጥያቄያቸውን እንደገና በማቅረብ መወዳደር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ ከአሁን በፊት የፕሮጀክት ሃሳብ አቅርበናል በማለት የምትጠባበቁ ባለሃብቶች/ድርጅቶች/ በዚህ ውድድር ተሳታፊ መሆን ከአልቻላችሁ ለምታነሱት ጥያቄ ቢሮው ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡
የኘሮጀክት ሃሳብ (Business plan) እና ሌሎች ጠቃሚ ማስረጃዎችን ቢቻል የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት እና የባለሀብቱ ፊርማ ተፈርሞበት ለአብክመ ገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ቢሮ የገጠር መሬት ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 2-19 በስራ ሰዓት መቅረብ ይኖርበታል፡፡
የውድድሩ ውጤት የምዝገባው ጊዜ በተጠናቀቀ በ30 የስራ ቀናት ውስጥ አሽናፊዎችን እና ውጤታቸውን በተቋሙ የውሰጥ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
በውጤቱ ቅሬታ ያለው አመልካች ካለ ጊዜያዊ ውጤቱ በተገለጸ በአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ቅሬታውን በጽሁፍ ለአብክመ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ማቅረብ ይችላል፡፡
አሸናፊ የሆነው ባለሃብት/ድርጅት/ ውጤቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ30 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ካልያዘ መብቱን መጠቀም እንዳልፈለገ ተቆጥሮ በነጥብ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አሸናፊ ባለሃብት ወይም ድርጅት ውል እንዲወስድ ይደረጋል፡፡
ቢሮው ውድድሩን እንደ አሰፈላጊነቱ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ከባለሃብት ተመልሰው ለውድድር የወጡ መሬቶች በካሳ ህጉ መሰረት ካሳ የሚያስከፍል ንብረት /ግንባታ፣አት/ፍራፍሬ እና መሰል ንብረቶች/ ካሉ አሸናፊው ግለሰብ/ድርጅት በካሳ ህጉ መሰረት ውል ከመውሰዱ በፊት ተገቢውን ካሳ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
በ2012 ዓ. ም በሰባት ዞኖች በመሬት ባንክ የሚገኝና ለባለሃብት ለማስተላለፍ የቀረበ የእርሻ ኢንቨስትመንት መሬት ዝርዝር














የአብክመ የገጠር የመሬት አስተዳደና አጠቃቀም ቢሮ
_______________________________
Category : Land and Lease
Posted Date : በኩር ሰኞ መጋቢት 14 ቀን 2012
Deadline :2020-04-23