Lease 01

Lease 01


የ አንደኛ ዙር የመሬት ሽያጭ ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ ደ/ወሎ ዞን በደላንታ ወረዳ የወገልጤና ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 (ሀ እስከ ሠ መሰረት በወገልጤና ከተማ ውስጥ የሚገኙ

ለመኖሪያ ከታደሰ ጌቶ ቤት ጎን G+1 እና በላይ ደረጃውን የጠበቀ መኖሪያ
ከተስፋ ካሴ ቤት ጎን G+1 እና በላይ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል
ኦፓል ማዕከል ጎን G+4 እና በላይ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል
ከተስፋ ዘገየ ቤት አካባቢ (G+2) እና በላይ ደረጃውን የጠበቀ ንግድ
ስለሆነም በጨረታ ላይ በመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ ተጫራቾች

የጨረታ ሰነዱን በወገልጤና ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ የኢትዮ ብር 600 / ስድስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላል ፤
ተጫራቾች ቦታዎች በሚገኙበት አካባቢ የቦታዎችን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ ፣
ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ዝርዝር መሰረት መሆን ይኖርበታል ፤
አንድ ተጫራች በአንድ ቦታ ላይ ከአንድ በላይ የጨረታ ሰነድ መግዛት አይችልም ፤
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ፖስታዋና እና ኮፒ በማድረግ በወገልጤና ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 11 ፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፤
ጨረታው በ2012ዓም ይህ ጨረታ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11 ኛው ቀን 4 ፡00 ሰዓት ላይ ማዘጋጃ ቤት ግቢ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፤
የጨረታ አሸናፊው የሚሰራው የግንባታ ሁኔታ የህንፃ አዋጅ መመሪያን መሰረት አድርጎ አብዛኛውን የቦታ መጠን በግንባታ መሸፈን ይጠበቅበታል፤
ተጫራቾች የጨረታ ማስገቢያ CPO የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በመነሳት የሚገኘውን ውጤት ከ5 በመቶ ያላነሰ በተቋሙ የዝግ አካውንት ቁጥር በማስገባት በባንክ የተመሰከረለትን ሰነድ ዋጋ እና ሃሳብ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም ከአምስት በመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ጨረታ ከውድደር ይሰረዛል፡፡
ቦታውን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት መ/ቤቱ በሚመድባቸው አስጎብኚዎች ቦታዎችን መመልከት ይችላል፡፡
ተጫራቹ በህግ አግባብ ለአካለ መጠን የደረሰ ስለመሆኑ ከሚኖርበት የአስተዳደር እርከን/ቀበሌ የታደሰ መታወቂያ ማቅረብ የሚችል
ተጫራቾች ቀደም ሲል በከተማው ውስጥ በምሪትም ይሁን በጨረታ አሰራር ለድርጅት አገልግሎት ቦታ በስዶ በአግባቡ በተዋዋለው የግንባታ ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ ያላለማ ወይም ቦታውን ወስዶ ግንባታ ሳያጠናቀቅ ለሶስተኛ አካል ያስተላለፈ አለመሆኑ ሲረጋገጥ
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር: 033 335 01 82 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ መ/ ቤቱ

በአብክመ ደ/ ወሎ ዞን በደላንታ ወረዳ የወገልጤና ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት





_______________________________
Category : Land and Lease, Sale.

Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 17 ፥2012
Deadline :2020-04-04

Report Page