Lab gedio fin2

Lab gedio fin2


በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መ/የጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በ2012 በጀት ዓመት ለጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ አገልግሎት የሚውል የትምህርት መርጃ ኬሚካል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ስመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቶች፡-

በ2012 በጀት ዓመት የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፤
የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፤
የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
ከላይ በዝርዝር የተቀመጠውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓ ት የማይመለስ ብር 50.00 / ሃምሳ ብር/ በመ ክፈል ከጌዴኦ ዞን ፋይ/ኢኮል/መምሪያ ግዥና ንብ/አስ/ዋ/ሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል። ቫትን ያላከተተ ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ይቆጠራል።
እያንዳንዱ ተጫራች የጨረ ታ ማስከበሪያ 5,000.00 / አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተ ረጋገጠ CPO ሲፒኦ፣ ከታውቀ ባንከ የሚሰጥ የክፍያ መዘዣ ቼክ ወይም በባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ አይቻልም።
ጨረታ ያሸነፈ ተጫራች ባሸነፋባቸው የዕቃ ዝርዝር መሠረት አሸናፊነታቸው ከተገለጸ በ7 /ሰባት/ ቀናት ውስጥ ከመ/ቤቱ ጋር የውል ስምምነት መፈራረም ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች እቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋና ዓይነት በመለየት በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ሞልተው አንድ ኦርጅናል ሰነድ እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ ካሸጉ በኋላ በሲፒኦ ጋር በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይገባቸዋል።
ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ በሚቆጠር በ15 ኛው ቀን ጠዋት የጨረታው ሳጥን በ4 ፡00 ሰዓት ታሽጎ 4 ፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ስለሆነም ተጫራቾች በዕለቱ ከጠዋቱ 2 ፡30 ሰዓት እስከ 4 ፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስ ጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይካሄዳል።

በኦርጅናል ሰነድ ላይ የሚደረግ ማናቸውም ስርዝ ድልዝ በሚነበብ መልኩ በድጋሚ ተጽፎ መፈረም ይኖርበታል።

የጨረታው ሳጥን የሚገኘው ጊዴኦ ዞን ፋይ/ኢኮ/ል/መምሪያ ቅጥር ግቢ ግዥና ንብ/አስ/ዋና ሥራ ሂደት ነው።
ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው ያሸነፉበትን ዕቃዎች ጌዴኦ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ የማጓጓዣ፣ የማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ ችለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 046-31-01-08 መደወል ይችላሉ።

በጌዲኦ ዞን ፋይ/ ኢኮ/ ል/ መምሪያ የግዥና ንብ/ አስ/ዋና ሥራ ሂደት

ዲላ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 23 ቀን 2012
Deadline: June 14, 2020


© walia tender

Report Page