#JawarMohammed

#JawarMohammed

By Tikvah-Ethiopia


በረሃብ አድማ ዛሬ 18ኛ ቀናቸውን የያዙት አነአቶ ጃዋር መሃመድ :

እነ አቶ ጃዋር ፥ አቶ በቀለ ገርባ እና ሌሎችም ፥ "እስር ቤቶች በኦሮሞ ልጆች ተሞልተዋል ፣ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ፣ የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲ ፅ/ቤቶች ተከፍተው በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩ ይደረግ፣ ገዢው ፓርቲ በኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ የሚያደርገውን ማዋከብ እና ጫና ያቁም ሌሎችም የምናነሳቸው ጥያቄዎች መልስ ይሰጣቸው" በሚል የጀመሩት የረሃብ አድማ ዛሬ 18 ቀን ሞልቶታል።

በረሃብ አድማው እየተሳተፉ ያሉት እስከ 20 የሚደርሱ ሲሆን ተዳክመው ሆስፒታል የገቡ በኃላም እኛ ጉሉኮስ እየወሰድን እና ህክምና እየተከታተልን ሌሎች አጋሮቻችን ረሃብ አድማ ላይ ሆነው ሆስፒታል ውስጥ እንቆይም በሚል ከሆስፒታል ወጥተዋል።

ከቀናት በፊት ከሆስፒታል ከወጡት መካከል አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ ሸምሰዲን ጣሃ፣ አቶ ቦና ቲቢሌ፣ አቶ አራፋት አቡበክር ይገኙበታል።


የእነ አቶ ጃዋር መሀመድ የግል ህክምና ቡድን የጤና ክትትል ማድረግ ማቆሙ :

በረሃብ አድማ ዛሬ 18 ቀናቸው ላይ የሚገኙት እነ አቶ ጃዋር መሀመድ የጤናቸውን ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ እየተገለፀ ይገኛል።

አሁን ላይ የግል ህክምና ቡድኑ ለእነአቶ ጃዋር መሃመድ የህክምና ክትትል ማድረግ አቁሟል።

የቡድኑ አስተባባሪ ዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ቡድኑ ከአርብ ምሽት ጀምሮ ክትትል ማቆሙን በመግለፅ አሁን ያሉበትን የጤና ሁኔታን እንደማያውቁ ገልፀዋል።

ቡድኑ የህክምና ክትትል ሊያቆም የቻለው አቶ በቀለ ገርባ ሆስፒታል ገብተው መታከም የነበረባቸው ቢሆንም የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር "ከላይ እየተደወለብን ነው" በማለት አስፈላጊው ህክምና ማድረግ ሳይቻል በመቅረቱ "የነሱ ሀኪም ናቸው" መባሉ ትርጉም ስለሌለው ክትትል አቁመናል ሲሉ ዶክተር ኢሊሊ ተናግረዋል።

የደም ግፊት ያለባቸው አቶ በቀለ አርብ ምሽት ላይ ወደግል ሆስፒታል ሊወሰዱ ሲሉ ወደመንግስት ሆስፒታል ካልወሰዳቹ መባላቸውን የገለፁት ዶ/ር ኢሊሊ ፥ ለዛ ደግሞ አቶ በቀለ ፍቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን ፤ ለህይወታችን ስለምንሰጋ በመንግስት ሆስፒታል መታከም አንፈልግም፤ ፍርድ ቤት በግል ሆስፒታል እንድንታከም ፈቅዶልናል ማለታቸውን ገልፀዋል።

የህክምና ቡድኑ ክትትል ያቆመው ተገዶ ነው ሲሉም ዶ/ር ኢሊሊ አሳውቀዋል።

ከእነ አቶ ጃዋር መሃመድ ጠበቃ መካከል አቶ ከድር ቡሎ የህምክናው ጉዳይ በተደጋጋሚ ውሳኔ የተሰጠበት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ነው የተጣሰው ብለዋል።

እስካሁን እየተነሳ ላለው ጉዳይ ከማረሚያ ቤት ኮማሽን ምላሽ አልተሰጠበትም።


የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ባለሞያዎች ጉብኝት :

አርብ እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ያሉበትን ሁኔታ የጎበኙት የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ባለሞያዎች አሁን ላይ ክትትል ካቆመው የህክምና ክትትል ቡድን እንዲሁም ከማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ጋር ውይይት ማድረጉ የተገለፀ ሲሆን ተገቢው ክትትል እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።


ለመሆኑ በረሃብ አድማ ምን ያህል ጊዜ መቆየት ይቻላል ?

የጤና ባለሞያዋ ዶክተር ኢሊሊ ጀማል ሰዎች የረሃብ አድማ ስላደረጉ በ 1፣ በ2 ወይም በ3 ሳምንት ሊሞቱ ይችላሉ ማላት እንዳልሆነ አስረድተዋል።

ዶ/ር ኢሊሊ ፥ "በረሃብ አድማ እስከ 45 ቀን የቆዩ ሰዎች አሉ፣ 60 ቀን ድረስም የቆየ ኬዝ አለ ከመሞቱ በፊት ፤ ሰውነታችን ምግብ መብላት ሲያቆም ከጉሉኮስ ሲያገኝ የነበረውን ኃይል ሌላ መንገድ ይፈልጋል እራሱን ለማቆየት ይታገላል። ግላይኮጅ፣ ፋት መጠቀም ይጀምራል ከሆነ ቀናት በኃላ ሰውነት ውስጥ ያለው ፋት ኃይል ለመቀየር ይሞክራል በህይወት እንዲቆዩ ያደርጋል። የሚያስፈራው ነገር ምንድነው በዚህ ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩ ቶክሲክ የሆነ የረጅም ጊዜ ጉዳት ሊያመጣ ይችላል"


[የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ፣ ጋዜጠኛ ስዩም ጌቱ፣ ዶክተር ኢሊሊ ጀማል፣ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ፣ ጠበቃ ከድር ቡሎ፣ ICRC]

Compiled By : Tikvah-Ethiopia

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

Report Page