Jani sale other aa3

Jani sale other aa3


የአገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢፌዴሪ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን እና የኢፌዴሪ እርቀ ሰላም ኮሚሽን በጋራ ለሚገለገሉበት

ባለ ሁለት ወለል ህንጻ ከእነ ቅፅር ግቢው የጥበቃ ፣ የፅዳት እና የአትክልት እንክብካቤ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት በጨረታው መወዳዳር የሚፈልጉና ማንኛውም ህጋዊ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላቸው አካላት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ህጋዊ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።
ተጫራቾች የአቅራቢዎችየአገልግሎት ዝርዝር ላይየተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ኖሯቸው በተሰጠው የንግድ ዘርፍ ብቻ መሳተፍ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የፋይናንሻልና የቴክኒካል ሰነድ በተናጠል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
ተጫራቾች 10,000.00/ አስር ሺ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ ቼክ (cpo) በአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ፅ/ቤት በባንክ የተረጋገጥ ቼክ በማሰራት ከጨረታ ሰነድ ጋር በማቅረብ መጫረት ይችላሉ:: ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው።

ተጫራቾች ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት እስከ ጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ::

ተጫራቾች በጨረታ ሳጥን ሰነድ ሲያስገቡ ኮፒ ጨምረው ማስገባት አለባቸው፡፡
ጨረታው በ10 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ይታሽጋል::

ጨረታው በ10 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎ ቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ስራ በሌለበት ቀን የመክፈቻ ጊዜ የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይሆናል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ 2ኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው ከአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ጽ/ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ የማይመለስ 100 ( አንድ መቶ ብር) በመክፈል ማግኘትይችላሉ::

**ኮሚሽን ጽ/ቤቶቹ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡***

አድራሻ ፦ሽሮሜዳ ከአሜሪካ ኤምባሲ አጠገብ በሚገኘው አዲሱ ቤተ መንግስት ( የድሮው አቅም ግንባታ ሚኒስቴር ግቢ ውስጥ ሁለተኛ ፎቅ)

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 126 11 96

የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ጽ/ ቤት

አዲስ አበባ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 22 ቀን 2012

Deadline: June 8, 2020


© walia tender

Report Page