It 4

It 4


stay home stay safe

በድጋሚ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ግጨ / ት / አመልፕ 02/2012
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የተሳትፏዊ አነስተኛ መስኖ ልማት ፕሮግራም ለ2012 ዓም ለፕሮግራሙ ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ

ዎርከ ስቴሽን ኮምፒዩተር፣
ኮምፒዩተሮች፣
የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎችና አክሰሰሪያቸውን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቶች ጨረታው ትሳተፉ ዘንድ ቢሮው ይጋብዛል፡
1. በዘርፉ አግባብነት ያለው እና በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድና ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉት

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ ያላቸው

3. የግዥ መጠኑ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ለሆነ ግዥ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን የተገናዘቡ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣

5.ተጫራቾች የዕቃው አይነት፣ የአምራቹን ሥም፣ የተመረተበትን ሀገር እና የሞዴል ቁጥር፣በዝርዝር መግለጫው(Specification) መሠረት ካታሎግ (Catalogue) ማቅረብ አለባቸው።

6.የሚገዙ የዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል

7.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ( ቢድ ቦንድ) ብር 10,602.00 በ ባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /Unconditional Bank Garmtee/ ማቅረብ አለባቸው፤

8.ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን በሁለት ፖስታዎች ማለትም በቴክኒካል ፖስታ እና በፋይናንሻል ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ማስገባት አለባቸው፡፡

8.1የቴክኒካል ፖስታ መያዝ (ማካተት) ያለሰት፡የዕቃዎቹ ዝርዝር መግለጫ (Specification) በዘርፉ እና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት፣ የማቅረቢያ ጊዜ፣ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ቀን እና ካታሎግ (Catalogue)
8.2 ፋይናንሻል ፖስታ መያዝ (ማካተት) ያለበት፡በዋጋ መሙያ ፎርም የተሞላ የእቃዎቹ ዋጋ እና የጨረታ ማስከበሪያ
9.እነዚህ የፋይናንሻል እኛ የቴከኒካል የመጫረቻ ሰነዶች ለእያንዳንዳቸው አንድ ኦርጅናል እና አንድ ቅጅ (ኮፒ) በማዘጋጀት በፖስታው ላይ ዋና (ኦርጅናል) ወይም ቅጅ (ኮፒ) መሆናቸውን የሚገልፅ ፅሑፍ በፖስታው ላይ በማስፈርና በጥንቃቄ በፖስታ ስማሸግ በግብርና ቢሮ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 12 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 17ኛው ቀን 08:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

10. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 / ሃምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 17ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በግብርና ቢሮ አንደኛ ፎቅ ፕሮጀክት ፋይናንስ ቢሮ ዘወትር በሥራ ሠዓት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፤

11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግብርና ቢሮ የግዥ/ ፋይ/ ንብ/ አስ/ ዳይሬክቶሬት በግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 12 ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ17 ኛው ቀን በ8 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8 ፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ዕለት የህዝብ በዓል፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 4 ፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 4 ፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡

12. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13 በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግብርና ቢሮ የግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት በግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 12 ድረስ በአካል ወይም በፋክስ ቁጥር 0582266431/0582265521 በመላክ ፤ በስልክ ቁጥር 0582265501 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ

መንግስት ግብርና ቢሮ

ባህር ዳር


Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 18 ቀን 2012

Deadline: May 6, 2020


©walia tender



Report Page