Ised tsehay insurance s.c 1

Ised tsehay insurance s.c 1

ADMIN 1 TADELE

የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን የካሣ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎችና የተለወጡ የተሽከርካሪ አካላትን እንዲሁም ሌሎች ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተሽከርካሪዎችንና የተሽከርካሪ አካላትን እንዲሁም ሌሎች ንብረቶችን መግዛት የሚፈልጉ ሁሉ ቃሊቲ ቶታል ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት በካፍደም ሲኒማ ወደ ዉስጥ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካን አለፍ ብሎ በሚገኘው የኩባንያዉ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች ማቆያ ቦታ በቆሙበት የግንቦት 17 ቀን 2012 ጀምሮ በመገኘትና በማየት የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ. ም. ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊትለፊት በሚገኘው ዋና መ/ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ መጫረት ይችላሉ።

በተጨማሪ 3 ቦቴ ታንከር መቀሌ የሚገኝ ስለሆነ ባሉበት መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች መጫረት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡
ጨረታው ግንቦት 29 ቀን 2012 ዓ. ም ከጧቱ 4:00 ሰዓት በኩባንያው ዋና መ/ቤት የሚከፈት ሲሆን ነገርግን ኮቪድ 19 ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል መንግስት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 ተግባራዊ ለማድረግ ሲባል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባልተገኙበት ይከፈታል።
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃ የመነሻ ዋጋውን 10% ( አስር በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው ለተሽከርካሪዎች ከብር 5,000.00 (አምስት ሺህ) እንዲሁም የተሽከርካሪ አካላት ላይ ከብር 500.00(አምስት መቶ) ማነስ የለበትም፡፡
ሌሎች ተጫራ ቾ ች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው።

ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃ የመነሻ ዋጋዉን 10% (አስር በተሽከርካሪዎችና ሌሎች አካላት ላይ ከጨረታው በፊት ዕዳዎች ቢኖሩ በኩባንያው ይሸፈናል:: በጨረታው ለተካተቱ ንብረቶች ከጨረታው በኋላ ያሉትን ማናቸውም ወጪዎች ገዥው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል።
የጨረታዉ አሽናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላሉ።

አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 06 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን መረከብ ዕቃዎቹንም ሙሉ በሙሉ ማንሳት አለባቸዉ። ይህ ካልሆነ ግን የጨረታው ውጤት የሚስረዝ ሆኖ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 111 97 71/70 ወይም 011 126 89 94 በመደወል ወይም ከላይ በተጠቀሰዉ ዋና መ/ቤት በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል።

ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ፀሐይ ኢንሹራንስ አ. ማ



Posted: ሪፖርተር ግንቦት 23 ቀን 2012

Deadline: June 5, 2020


© walia tender

Report Page