Ict sale comp deb attor 48

Ict sale comp deb attor 48


call 0919415260 for further information

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የደ / ብ / ብ / ሕ / ክ / መ / ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ መ / ቤት ከዚህ በታች የተጠቀሰውን ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የኔትወርክ መሳሪያዎች እና የዴስክ ቶፕ ኮምፒዩተሮች የኤሌክትሪክ መስጫ አካል /Power Supply/
በዚህም መሰረት

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ ያቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው።
ተጫራቾች የቴክኒክና የፋይናንሻል ሰነድ እያንዳንዱ በ 2 ኮፒ በተለያየ ሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ( ፖስታ ) ማቅረብ አለባቸው።
የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከመ / ቤቱ ግዢ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግንባር ቀርበው ወይም በህጋዊ ወኪል አማካኝነት በነፃ መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) በማካተት በሰም በታሸገ ኤቨሎፕ ( ፖስታ ) በማሸግ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ኛው ተከታታይ ቀን 4 ፡ 00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ በደ / ብ / ብ / ሕ / ክ / መ / ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ መ / ቤት ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 104 በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
የጨረታው ሳጥን በዚሁ ዕለት / በ 16 ኛው ቀን / ከጠዋቱ 4 ፡ 00 ሰዓት ላይ ይታሸግና በ 4 ፡ 05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 16 ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል።
የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸው ዕቃዎች መስሪያ ቤታችን ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ጨረታ ውጤት እስከሚገለጽ እና ይህ ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ እስከ 80 ቀን ድረስ የፀና ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ፡ - በስልክ ቁጥር፡ - 046-220-73-27/0911-53-01-66 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በደ / ብ / ብ / ሕክ / መንግስት የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

ሀዋሳ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 10 ቀን 2012
Deadline: June 3, 2020


© walia tender

Report Page