Ict omo micro 22

Ict omo micro 22


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶችን/ዕቃዎችን፡-

Antivirus with 3 year License
Firewal Forti Guard Service with 3 year License በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፦

ከላይ በተጠቀሱት ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ። የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin number/ ያላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
በፋይናንስ መሥሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበና የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀ ሰነድ መግዛት የሚችል ማንኛውም ተጫራች መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን ሰነዱን ከተቋም ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸን ዋናና ኮፒ ለየብቻ በሁለት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርጎ ዋናና ኮፒ ብለው በአንድ እናት ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ቴክኒካልና ፋይናንሻል ለየብቻ ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8 ሰዓት በፊት ብቻ ይሆናል፡፡ ጨረታው በ15 ኛው ቀን ከቀኑ 8 ፡00 ሰዓት ታሽጐ በ8 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ ን/ ጠ/ አገ/ ዳይሬክቶሬት 2 ኛ ፎቅ ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም 15 ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታ የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋ ጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ CPO ፣ በባን ክ ጋራንት ወይም በካሽ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊ የሆነ ድርጅት በተፈለገው ጊዜና ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ እስከ ዋና መ/ቤት ድረስ ማቅረብና ማስረከብ ይኖርበታል፡፡ በጨታው ለመሳተፍ የሚፈልግ/ጉ/አቅራቢ/ዎች ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር 046 212 52 14 ዘወትር በሥራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተቋሙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የተቋሙ አድራሻ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ
አድራሻ፡- ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሞቢል በሚወስደው መንገድ ከጠቅላይ ፍ/ ቤት አለፍ ብሎ፡፡

ሃዋሳ

የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ . ማ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 16 ቀን 2012

Deadline: June 8, 2020


© walia tender

Report Page