Ict debub 1

Ict debub 1


የእቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ መንግሥት የሴቶች ህጸናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የኔትዎርክ ዝርጋታ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

ተጫራቾች ለተሰማሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ያላቸው።
የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የተቀበሉትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 50 ( ሃምሳ ) ብር በመክፈል ከቢሮአችን ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ።
ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000 / አስር ሺህ ብር / በቢሯችን ስም በተዘጋጀና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ቢድ ቦንድ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት።
ተጫራቾች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው::
ተጫራች የጨረታ ሰነዳቸውን አስፈላጊውን መረጃ በማያያዝ ኦርጅናሉንና ኮፒውን በታሸገ ፖስታ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቢሯችን ለዚሁ ተግባር ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ማስገባት አለባቸው :: ሳጥኑም በ 15 ኛው ቀን በ 11 ፡ 00 ሰዓት ይታሸጋል።
ጨረታው በ 16 ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 8 ፡ 30 ሰዓት በቢሮአችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። 16 ኛው ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ የጨረታው ማስከበሪያ ገንዘብ ላላሸነፉት ድርጅቶች ወዲያውኑ ይመለሳል።
የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለጸለት ወደ ቢሯችን መጥቶ አስፈላጊውን የጨረታ ውል መፈረም አለበት። ይህን ባይፈጽም ቀደም ሲል ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
በክልሉ ግዥ አዋጅና መመሪያ ውስጥ ለአገር ውስጥ ልዩ አስተያየት የሚደረግላቸው አካላት በሚያቀርቡት ማስረጃ መሰረት ይስተናገዳሉ።
ቢሮአችን ጨረታውን አስመልክቶ የተሻለ አማራጨች ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-221-31 34

የደ/ ብ/ ብ/ ሕ/ ክ መንግሥት የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ




Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 12 ቀን 2012
Deadline: June 3, 2020


© walia tender

Report Page