INSA ict

INSA ict


የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ኢመደኤ ግልፅ ጨረታ ፕሮጀክት 05/2012

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የተለያዩ የእቃ ግዢዎችን በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፡

ሀ. በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገፅ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ወይም ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተሰጣቸውን የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

ለ. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ቫት፣ ቲን እና ከሀገር ውስጥ ገቢዎች ባለስልጣን የሚሰጥ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡

ሐ. በሚወዳደሩበት ዘርፍ የተሰማሩበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

መ. በአማርኛ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሠዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ማግስት ጀምሮ ከኤጀንሲው ፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡

ሠ. ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የጨረታ ሰነዱን በነፃ ማግኘት የሚችሉት ካቋቋማቸው አካል ማስረጃ ሲያቀርቡ ብቻ ሲሆን ደብዳቤ ሲያፅፉ የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ማስጠቀስ ይኖርባቸዋል፡፡

ረ. የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ CPO ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ አገልግሎት ዋስትና መሆን አለበት፡፡

ሰ. የጨረታ ማስከበሪያ መጠን እና ጨረታው የሚዘጋበት ቀን ቀጥሎ በሰንጠረዥ ተገልጿል፡፡

ሸ. ተጫራቾች ለሁሉም የግዥ ዓይነቶች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡

ቀ. ኤጀንሲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ አድራሻ፡- ሣር ቤት ብስራተ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሳይደርስ አዶት ህንፃ
አጠገብ አፍሪካ ኢንሹራንስ ታወር 1 ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 ፡፡
ስልክ ቁጥር 011-320-40-07/ 0113-71-71-14 ( የውስጥ መስመር 131/176)

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ


Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 20 ቀን 2012

Deadline: June 11, 2020


© walia tender

Report Page